SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

SBS
País Australia
Idioma AM
Episodios 900
Último 11.10.2026

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Episodios

  • "የተባበሩት መንግሥታት ብዙውን ጊዜ ግጭት ማስቀረት ላይ ስኬታማ ሆኖ አላየውም፤ ግጭት ከተፈጠረ በኋላ ቶሎ ይገባል" ሌተና ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል 11.10.2026 18m
    ሌተና ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል፤ እ.አ.አ. ከ2012-14 በተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ባን ኪሙን ለአቢዪ እንዲሁም ከ2014-16 ለደቡብ ሱዳን የተመድ ፀጥታ ኃይል አዛዥ ሆነው ተመድበው አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ መረጃ መምሪያ ዋና ኃላፊነት ሠርተዋል፤ በቅርቡም "የግጭት አዙሪት እና የአፍሪካ ቀንድ" በሚል ርዕስ መፅሐፍ ደርሰው ለአንባቢያን አበርክተዋል። ዳግም በተቀሰቀሰው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና የኢትዮጵያና ኤርትራን ወታደራዊ የግጭት አቅጣጫ አንስተው የሙያና የተሞክሮ ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።#sbsaudiopodcast
  • "በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ውጊያ መቀጠሉ የሚቀር አይመስለኝም፤ በማን የበላይነትና እንዴት ይቋጫል የሚለውን ወደፊት የምናየው ነው" ሌ/ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል 11.10.2026 17m
    ሌተና ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል፤ እ.አ.አ. ከ2012-14 በተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ባን ኪሙን ለአቢዪ እንዲሁም ከ2014-16 ለደቡብ ሱዳን የተመድ ፀጥታ ኃይል አዛዥ ሆነው ተመድበው አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ መረጃ መምሪያ ዋና ኃላፊነት ሠርተዋል፤ በቅርቡም "የግጭት አዙሪት እና የአፍሪካ ቀንድ" በሚል ርዕስ መፅሐፍ ደርሰው ለአንባቢያን አበርክተዋል። ዳግም በተቀሰቀሰው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና የኢትዮጵያና ኤርትራን ወታደራዊ የግጭት አቅጣጫ አንስተው የሙያና የተሞክሮ ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።#sbsaudiopodcast
  • ርእሰ አድባራት ደብረሰላም መድሀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በአውስትራሊያ ያስገነባውን ሁለገብ ሕንጻ አስመረቀ 11.10.2026 15m
    ርእሰ አድባራት ደብረሰላም መድሀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በአውስትራሊያ ያስገነባውን ሁለገብ ሕንጻ በትናንትናው እለት አስመርቋል። የደብረሰላም ሜልበርን መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን በአውስትራሊያ የመጀመሪያ እና በአባላት መጥንም ሆነ ባገልግሎት እየሰፋ በመሄዱ ፤ የአውስትራሊያና ኒውዝላንድ ሐገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት አቡነ ሉቃስ ከሀገር አሜሪካ " ርእሰ አድባራት ደብረሰላም መድሀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በአውስትራሊያ " እንዲባል ወስነዋል። መልእክታቸውም በብጹእ አቡነ ጴጥሮስ የኒውዬርክና አካባቢው ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በኩል ተላልፏል። በምረቃው ስነ ስርአት ላይ ብጹእ አቡነ ጴጥሮስ የኒውዬርክና አካባቢው ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፤ ብፁዕ አቡነ ዬሴፍ የሲዳማ ሐገረ ስብከት ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ፤ በአውስትራሊያና ኒውዝላድ ያሉ የየደብሩ አስተዳዳሪዎችና ምእመናን ፤ የግብጽ ኮፕት ቤተክርስቲያን አባቶች፤ የፓርላማ አባላት ፤ ሚኒስትሮች ፤ የአካባቢው ከንቲባዎች እና ካውንስለሮች ተገኝተዋል።#sbsaudiopodcast
  • በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የቀጥታ ጦርነት ጅማሮ ስጋት ንሯል፤ በትግራይ የጦር ኃይሎች እንቅስቃሴ ቀጥሏል 09.10.2026 5m
    ኢትዮጵያ የኤርትራ ወታደሮች ከግዛቷ በአስቸኳይ እንዲወጡ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አመለከተች#sbsaudiopodcast
  • "ኢትዮጵያ በአድዋ ጦርነት በራሷ ምድር አጥቂ እንጂ ተከላካይ አልነበረችም" ዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን 07.10.2026 26m
    ዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን፤ በኦስቲን ኮሙዩኒቲ ኮሌጅ ጂ አይ ኤስ ተባባሪ ፕሮፌሰር፤ ሰሞኑን "ከፑንት እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ" በሚል ርዕስ በዶ/ር ግርማ አውግቸው አርታኢነትና በሴማዊ ጥናቶች መካነ ተቋም አሳታሚነት ለሕትመት በበቃው መፅሐፍ ላይ "የአድዋ ድልና ትርክት በጂኦግራፊያዊ ዕይታ ሲፈተሽ" በሚል ርዕሰ መጠሪያ ስላቀረቡት የመጣጥፋቸው ጭብጦች ይናገራሉ።#sbsaudiopodcast
  • ኢትዮጵያ በዓባይና በቀይ ባሕር ላይ ያላትን ጥቅም ዳግም አስገነዘበች፤ በትግራይ ውጊያው ቀጥሏል 06.10.2026 11m
    ዳግም በትረ ስልጣናቸውን የተረከቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመመስረቻ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ይፋ ንግግር፤ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት መንግሥታቸው ሁነኛ ትኩረት የሚሰጥባቸውን ዋነኛ አቅጣጫዎች አመላከቱ።#sbsaudiopodcast
  • Why power is split, and how that protects you | How Australia Works - ስልጣን ስለምን ነው የተከፋፈለው፤ እንደምንስ ነው ለእርስዎ ጥበቃ የሚያደርገው | አውስትራሊያ እንደም እንደምትተገብር 06.10.2026 7m
    After receiving a fine for not wearing his motorbike helmet correctly, Hugo decides to have the matter heard in court. His story explains how Parliament, government and the courts have different roles, and how some official decisions can be questioned. - የሞተር ብስክሌት ሔልሜት በአግባቡ አላደረግክም በሚል አስባብ መቀጮ ሲደርሰው፤ ሁጉ ጉዳዩ ለችሎት ስሚ እንዲቀርብለት ከውሳኔ ላይ ደረሰ። የእሱ ታሪክ ፓርላማ፣ መንግሥትና ፍርድ ቤቶች ስላሏቸው የተለያዩ ሚናዎችና እንደምን የተወሰኑ ይፋ ውሳኔዎች ጥያቄ ሊቀርብባቸው እንደሚችል ግንዛቤ ያስጨብጣል።How Australia Works is an SBS podcast that uses real stories and clear explanations to help you understand how government work in Australia, how laws are made and changed, and how you can have a say. Listen to the series and find shorter versions in 60 languages on the How Australia Works main page. - አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር የ SBS ፖድካስት አውስትራሊያ ውስጥ የአውስትራሊያ መንግሥት እንደምን እንደሚንቀሳቀስ፣ ሕጎች እንደምን እንደሚቀረፁና እንደሚለወጡ፤ እርስዎም አተያይዎን እንደምን እንደሚያጋሩ እውነተኛ ታሪኮችን በመንቀስ ግንዛቤን እንዲጨብጡ የሚያግዝዎ ነው። ተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶቹን ያድምጡ፤ ቅንጭብ ዝግጅቶቹንም በ60 ቋንቋዎች አውስትራሊያ እንደምን እንደምተገብር ዋነኛ ገፅ ላይ ያግኙ።
  • የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና አጋሮቹ መቀሌን መቆጣጠር 05.10.2026 8m
    በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል እየበረታ ያለው ግጭት ያሳሰባት ዩናይትድ ስቴትስ ሁለቱ ሀገራት ከግጭት ተቆጥበው ወደ ንግግር እንዲመለሱ አሳሰበች#sbsaudiopodcast
  • የአውስትራሊያ መንግሥት የከሰል ማዕድን ቁፋሮ ማስፋፋት በቅድመ COP31 ጉባኤ ተቃውሞ እየጠበቀው ነው 05.10.2026 5m
    አውስትራሊያ ራሷን በሰከነ የምጣኔ ሃብት ሀገርነት፣ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ መሪነትና የታዳሽ ኃይል ማዕከልነት ለማስተዋወቅ ወጥናለች#sbsaudiopodcast
  • የአውስትራሊያ የቋንቋ ለውጥ የአዲሱ የSBS ክለሳ ቀራጭ ይሆናል 05.10.2026 8m
    በርካታ ከአንድ ቋንቋ በላይ ተናጋር የሆኑ ፍልሰተኛ ቤተሰቦች የSBS ሬዲዮ የተለያዩ ቋንቋ ፕሮግራሞችን ከማድመጥ የተያያዙ የግል ትዝታዎችና ልዩ ትስስሮሽ አሏቸው። እነዚህ ፕሮግራሞች ባለፉት ዓመታት ተለውጠዋል፤ ተስፋፍተዋል። እናም አሁን SBS በዘመናዊቷ አውስትራሊያ የሚታዩትን የማኅበረሰብ ለውጦችና ፍላጎቶችን ለማንፀባረቅ የቋንቋ አገልግሎቶቹን ክለሳ ለማካሄድ በመሰናዶ ላይ ይገኛል። ለክለሳውም የሕዝባዊ ምክክር ጊዜ ይኖራል። ይህም ከመስከረም 25 እስከ ጥቅምት 3 ድረስ ይከናወናል።#sbsaudiopodcast
  • #119 Talking about hay fever (Med) - #119 Talking about hay fever (Med) 01.10.2026 10m
    Learn English useful for talking about hay fever. Practise everyday phrases for describing symptoms, talking about medicine, and responding kindly when someone has hay fever. - ስለ ሄይ ፊቨር (hay fever) ለመናገር እንግሊዝኛን ይማሩን ይጠቀሙ። የሕመም ምልክቶችን ገላጭ ስለሆኑ አዘቦታዊ ቃለ ሐረጎች፣ ስለ መድኃኒትና በሄይ ፊቨር የታመመን ሰው በትሁት አንደበት ማናገርን ይለማመዱ።Keep practising the phrases from this episode and test what you’ve learned with our quiz here. - ቃለ ሐረጎችን መማርን ከእዚህ ተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶች ይለማመዱና የተማሩትን እዚህይፈትኑ።
  • የአውስትራሊያ መንግሥት ቬይትናም ውስጥ አንድ ለእሥር የተዳረገ ዜጋውን እንዲያስፈታ ግፊት እየተደረገበት ነው 30.09.2026 7m
    የአውስትራሊያ የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የብሔራዊ ባንክ የወለድ መጠን ጭማሪ ለመንግሥት የምጣኔ ሀብት አስተዳደሩ ላይ ለውጥ እንዲያካሂድ የማስጠንቀቂያ ደወል እንደሁ አመላከተ#sbsaudiopodcast
  • "ኢሬቻ ለእግዚአብሔር ምስጋና የምናቀርብበት እንጂ ከሃይማኖት ጋር ግንኙነት የለውም፤ መልካም የኢሬቻ በዓል" አቶ አብደታ ሆማ 30.09.2026 13m
    አቶ አብደታ ሆማ፤ የቪክቶሪያ ኢሬቻ በዓል አስተባባሪ ኮሚቴ ፕሬዚደንት፤ የኢሬቻ ክብረ በዓል ሜልበርን አውስትራሊያ ውስጥ እንደምን መከበር እንደጀመረና ዘንድሮም እንደምን ተከብሮ እንደዋለ ይናገራሉ።#sbsaudiopodcast
  • " 'ኢሬቻ ከጨለማ አውጥተኸን ለብርሃን ስላደረስከን እናመሰግናለን' የሚባልበት ቀን ነው" ወ/ሮ ይፍቱ ሚደቅሳ 29.09.2026 8m
    የኢሬቻ በዓል 2026 በሜልበርን Wilson Botanic Park እሑድ መስከረም 17 / ሴፕቴምበር 27 በኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላትና ተጋባዥ እንግዶች ተከብሮ ውሏል። ከታዳሚ የማኅበረሰብ አባላት እስከ አባ መልካ የበዓሉን አከባበር አስመልክተው አተያዮቻቸውን ያጋራሉ።#sbsaudiopodcast
  • Who really runs Australia, and where you fit in | How Australia Works - በእርግጥ አውስትራሊያን የሚያስተዳድረው ማን ነው? የእርስዎ ሥፍራስ የት ነው? | አውስትራሊያ እንደምን እንደምተገብር 29.09.2026 8m
    Do you know who can help you with a business permit, a rental problem or family support? Through the stories of Fedele, Carol and Abeer, learn how Australia’s three levels of government work. Find out what local, state or territory, and federal governments are responsible for and where to turn for help. - የንግድ ፈቃድ ለማግኘት፣ የቤት ኪራይ ችግርዎን ለመፍታት ወይም የቤተሰብ ድጋፍ ለማግኘት ማን ሊያግዝዎ እንደሚችል ያውቃሉን? ከፌደል፣ ካሮልና አቢር ታሪኮች የአውስትራሊያ ሶሶት የመንግሥት ደረጃዎች እንደምን እንደሚሠሩ ይረዱ። የአካባቢ፣ ክፍለ ሃገር ወይም ግዛትና የፌዴራል መንግሥታት ኃላፊነት ምን እንደሆነና ለእገዛ ወዴት ማምራት እንዳለብዎት ይወቁ።How Australia Works is an SBS podcast that uses real stories and clear explanations to help you understand how government work in Australia, how laws are made and changed, and how you can have a say. Listen to the series and find shorter versions in 60 languages on the How Australia Works main page. - አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር የ SBS ፖድካስት አውስትራሊያ ውስጥ የአውስትራሊያ መንግሥት እንደምን እንደሚንቀሳቀስ፣ ሕጎች እንደምን እንደሚቀረፁና እንደሚለወጡ፤ እርስዎም አተያይዎን እንደምን እንደሚያጋሩ እውነተኛ ታሪኮችን በመንቀስ ግንዛቤን እንዲጨብጡ የሚያግዝዎ ነው። ተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶቹን ያድምጡ፤ ቅንጭብ ዝግጅቶቹንም በ60 ቋንቋዎች አውስትራሊያ እንደምን እንደምተገብር ዋነኛ ገፅ ላይ ያግኙ።
  • You are already inside the system | How Australia Works - ከወዲሁ ሥርዓተ ስሪቱ ውስጥ ተካትተዋል | አውስትራሊያ እንደምን እንደምተገብር 29.09.2026 4m
    How do Australia’s governments, laws and public services affect your everyday life? Through real stories, this introduction to the series shows you where to start when you need information and support, and how to question a decision. - የአውስትራሊያ መንግሥታት፣ ሕጎችና ሕዝባዊ አገልግሎቶች እንደምን የእርስዎ የዕለት ተዕለት ሕይወት ላይ ተፅዕኖ አንዳላቸው? እውነተኛ ታሪኮችን ተመርኩዞ፤ ይህ መንደርደሪያ መረጃንና ድጋፍን ሲሹ፤ ሲልም በውሳኔ ላይ ጥያቄን ለማንሳት ከተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶቹ ውስጥ ከየት መነሳት እደሚችሉ አመላካች ነው።How Australia Works is an SBS podcast that uses real stories and clear explanations to help you understand how government work in Australia, how laws are made and changed, and how you can have a say. Listen to the series and find shorter versions in 60 languages on the How Australia Works main page. - አውስትራሊያ እንደምን እንደምተገብር የ SBS ፖድካስት አውስትራሊያ ውስጥ የአውስትራሊያ መንግሥት እንደምን እንደሚንቀሳቀስ፣ ሕጎች እንደምን እንደሚቀረፁና እንደሚለወጡ፤ እርስዎም አተያይዎን እንደምን እንደሚያጋሩ እውነተኛ ታሪኮችን በመንቀስ ግንዛቤን እንዲጨብጡ የሚያግዝዎ ነው። ተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶቹን ያድምጡ፤ ቅንጭብ ዝግጅቶቹንም በ60 ቋንቋዎች አውስትራሊያ እንደምን እንደምተገብር ዋነኛ ገፅ ላይ ያግኙ።
  • የተባበሩት መንግሥትታ ድርጅት፣ የአፍሪካ ኅብረትና የውጭ ሀገር መንግሥታት በሰሜን ኢትዮጵያ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ስጋቶቻቸውን ገለጡ 28.09.2026 12m
    በ 660 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የሚገነባው የኢትዮ - ጂቡቲ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ዝርጋታ በሁለት ዓመታት ውስጥ ተጠናቅቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ ተገለጠ#sbsaudiopodcast
  • የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት የበጀት ጉድለት ከተገመተው ያነሰ ሆኗል 28.09.2026 6m
    አምስት ግለሰቦች ዩናይትድ ስቴትስ ኢራን ላይ ለጥቃት በተጠቀመችበት አንድ የእንግሊዝ አየር ኃይል ጦር ሠፈር አካባቢ በሽብር ተግባር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ#sbsaudiopodcast
  • " እንኳን ለደመራ እና የመስቀል በአል በሰላም አደረሳችሁ " - መላከ አርያም ቀሲስ ተስፋ ህሩይ 27.09.2026 4m
    መላከ አርያም ቀሲስ ተስፋ ህሩይ በሜልበርን የደብረሰላም መድሃኒአለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ፤ የዘንድሮውን በአል አስመልክተው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።#sbsaudiopodcast
  • ኒውዮርክ ላይ የተከፈተው የተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ የሞቁና የከረሩ አተያዮች ገጠሙት 23.09.2026 7m
    አንድ የሜልበርን ነዋሪ በሽብር ተግባር ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ዋለ#sbsaudiopodcast

Popular en

Este podcast también aparece en las listas de podcasts de estos países.