SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
SBS
0
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
エピソード
-
"ኢትዮጵያና ኤርትራ አፋሮችን ጨምረው ለ99 ዓመት የሚዘልቅ የታላቋ አሰብ ባለስልጣን በውል ሊያቋቁሙ ይገባል" አቶ ኅሩይ ተድላ ባይሩ 17.10.2026 26分አቶ ኅሩይ ተድላ ባይሩ፤ የቀድሞው የኤርትራ ነፃ አውጪ ግንባር (ELF) ምክትል ፕሬዚደንትና "Eritrea and Ethiopia: A front row look at issues of conflict and the potential for a peaceful resolution" መጽሐፍ ደራሲ፤ የአሰብና ሌሎችንም በኤርትራ ያሉ ሊያድጉ የሚችሉ ወደቦችንና የኢትዮጵያና ኤርትራን አሳሳቢ የጦርነት ዕሳቤ አስመልክተው ይናገራሉ። የሰላማዊ መፍትሔ ምክረ ሃሳቦቻቸውን ያጋራሉ።#sbsaudiopodcast -
የውይይት መድረክ፤ የአውስትራሊያ ሚና ለሰሜን ኢትዮጵያና ኢትዮ-ኤርትራ ግጭትና ውጥረት ቅነሳ 16.10.2026 13分ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደስ (ኢትዮጵያዊት - አውስትራሊያዊት)፣ አቶ ልዑል ፍስሃ (ኢትዮጵያዊ - አውስትራሊያዊ)፣ እና አቶ ዮሐንስ ወንድማገኝ (ኤርትራዊ - አውስትራሊያዊ) የአውስትራሊያ መንግሥት ለኢትዮጵያና ኤርትራውያን አውስትራሊያውያን፤ ዐልፎም ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎችን በማሳደር ረገድ ለሰላም መስፈን እንደምን የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ያላቸውን ግለ አመለካከቶች ያጋራሉ።#sbsaudiopodcast -
የውይይት መድረክ፤ የኢትዮ-ኤርትራ ሉዓላዊነት፣ ብሔራዊ ጥቅምና የወደብ አጠቃቀም 16.10.2026 18分ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደስ (ኢትዮጵያዊት - አውስትራሊያዊት)፣ አቶ ልዑል ፍስሃ (ኢትዮጵያዊ - አውስትራሊያዊ)፣ እና አቶ ዮሐንስ ወንድማገኝ (ኤርትራዊ - አውስትራሊያዊ) የኢትዮጵያና ኤርትራን ብሔራዊ ጥቅም፣ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ማስከበርን በተመለከተ አተያዮቻቸውን ያንፀባርቃሉ።#sbsaudiopodcast -
የውይይት መድረክ፤ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና የኢትዮጵያ - ኤርትራ ወታደራዊ ውጥረት ማኅበረሰባዊ የሥነ ልቦና ጫና 15.10.2026 20分ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደስ (ኢትዮጵያዊት - አውስትራሊያዊት)፣ አቶ ልዑል ፍስሃ (ኢትዮጵያዊ - አውስትራሊያዊ)፣ እና አቶ ዮሐንስ ወንድማገኝ (ኤርትራዊ - አውስትራሊያዊ) በሰሜን ኢትዮጵያ ተከስቶ ባለው ጦርነት፤ እንዲሁም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ከርረው ያሉት ዲፕሎማሲያዊና ወታደራዊ ውጥረቶች በሀገረ አውስትራሊያ ነዋሪ በሆኑ ኢትዮጵያውንና ኤርትራውያን፤ ትውልደ - ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የማኅበረሰብ አባላት ላይ ስላሳደራቸውና ሊያሳድሯቸው ስለሚችሉት ስነ ልቦናዊ ተፅዕኖዎች ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።#sbsaudiopodcast -
በርካታ አውስትራሊያውያን መንግሥት በቤት ኪራይ ክፍያ ጭማሪ ገደብ ላይ ጣልቃ ቢገባ እንደሚሹ ገለጡ 14.10.2026 6分በራፕ ኮከቡ ቱፓክ ሻኩር ግድያ የተከሰሰው ግለሰብ የ40 ዓመት እሥራት ተበየነበት#sbsaudiopodcast -
የተባበሩት መንግሥትታ ድርጅት የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ዓለም አቀፋዊ ይዘት እንዳይኖረው ስጋት ያደረበት መሆኑን ገለጠ 14.10.2026 11分በኢትዮጵያ በዓመት 600 ቶን ወርቅ የማጣራት አቅም ያለው ፋብሪካ ተመረቀ#sbsaudiopodcast -
ሕጎች እንዴት ነው የሚቀረፁት፤ እርስዎ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩትስ እንደምን ነው | አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር 13.10.2026 9分ሕጎች አውስትራሊያ ውስጥ የሚቀረፁት እንደምን ነው? በዉራንጄሪው አረጋዊ አጎት ዴቭ ዋንዲን አማካይነት የቢራራንግ እንዲሁም ያራ ወንዝ በመባል የሚታወቀውን ወንዝ ታሪክ ይቅሰሙ፤ እንደምን ፅንሰ ሃሳብ ለረቂቅ ድንጋጌነት እንደበቃ፤ በቪክቶሪያ ፓርላማ ይሁንታን እንዳገኘና ንጉሣዊ ፅድቅ ተችሮት ለሕግነት እንደበቃ።አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገበር እውነተኛ ታሪኮችን ነቅሶ፤ አውስትራሊያ ውስጥ መንግሥት እንደምን እንደሚሠራ፣ ሕጎች እንደምን እንደሚቀረፁና እንደሚሻሻሉ፣ እንደምን አተያዮን ማጋራት እንደሚችሉ ግንዛቤን የሚያስጨብጥዎ የSBS ፖድካስት ነው። ተከታትይ ክፍለ ዝግጅቶችንና አጭር ክፍለ ዝግጅቶችን በ60 ቋንቋዎች አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር ዋነኛ ገፅ ላይ አግኝተው ያድምጡ። -
"የተባበሩት መንግሥታት ብዙውን ጊዜ ግጭት ማስቀረት ላይ ስኬታማ ሆኖ አላየውም፤ ግጭት ከተፈጠረ በኋላ ቶሎ ይገባል" ሌተና ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል 11.10.2026 18分ሌተና ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል፤ እ.አ.አ. ከ2012-14 በተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ባን ኪሙን ለአቢዪ እንዲሁም ከ2014-16 ለደቡብ ሱዳን የተመድ ፀጥታ ኃይል አዛዥ ሆነው ተመድበው አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ መረጃ መምሪያ ዋና ኃላፊነት ሠርተዋል፤ በቅርቡም "የግጭት አዙሪት እና የአፍሪካ ቀንድ" በሚል ርዕስ መፅሐፍ ደርሰው ለአንባቢያን አበርክተዋል። ዳግም በተቀሰቀሰው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና የኢትዮጵያና ኤርትራን ወታደራዊ የግጭት አቅጣጫ አንስተው የሙያና የተሞክሮ ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።#sbsaudiopodcast -
"በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ውጊያ መቀጠሉ የሚቀር አይመስለኝም፤ በማን የበላይነትና እንዴት ይቋጫል የሚለውን ወደፊት የምናየው ነው" ሌ/ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል 11.10.2026 17分ሌተና ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል፤ እ.አ.አ. ከ2012-14 በተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ባን ኪሙን ለአቢዪ እንዲሁም ከ2014-16 ለደቡብ ሱዳን የተመድ ፀጥታ ኃይል አዛዥ ሆነው ተመድበው አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ መረጃ መምሪያ ዋና ኃላፊነት ሠርተዋል፤ በቅርቡም "የግጭት አዙሪት እና የአፍሪካ ቀንድ" በሚል ርዕስ መፅሐፍ ደርሰው ለአንባቢያን አበርክተዋል። ዳግም በተቀሰቀሰው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና የኢትዮጵያና ኤርትራን ወታደራዊ የግጭት አቅጣጫ አንስተው የሙያና የተሞክሮ ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።#sbsaudiopodcast -
ርእሰ አድባራት ደብረሰላም መድሀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በአውስትራሊያ ያስገነባውን ሁለገብ ሕንጻ አስመረቀ 11.10.2026 15分ርእሰ አድባራት ደብረሰላም መድሀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በአውስትራሊያ ያስገነባውን ሁለገብ ሕንጻ በትናንትናው እለት አስመርቋል። የደብረሰላም ሜልበርን መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን በአውስትራሊያ የመጀመሪያ እና በአባላት መጥንም ሆነ ባገልግሎት እየሰፋ በመሄዱ ፤ የአውስትራሊያና ኒውዝላንድ ሐገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት አቡነ ሉቃስ ከሀገር አሜሪካ " ርእሰ አድባራት ደብረሰላም መድሀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በአውስትራሊያ " እንዲባል ወስነዋል። መልእክታቸውም በብጹእ አቡነ ጴጥሮስ የኒውዬርክና አካባቢው ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በኩል ተላልፏል። በምረቃው ስነ ስርአት ላይ ብጹእ አቡነ ጴጥሮስ የኒውዬርክና አካባቢው ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፤ ብፁዕ አቡነ ዬሴፍ የሲዳማ ሐገረ ስብከት ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ፤ በአውስትራሊያና ኒውዝላድ ያሉ የየደብሩ አስተዳዳሪዎችና ምእመናን ፤ የግብጽ ኮፕት ቤተክርስቲያን አባቶች፤ የፓርላማ አባላት ፤ ሚኒስትሮች ፤ የአካባቢው ከንቲባዎች እና ካውንስለሮች ተገኝተዋል።#sbsaudiopodcast -
በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የቀጥታ ጦርነት ጅማሮ ስጋት ንሯል፤ በትግራይ የጦር ኃይሎች እንቅስቃሴ ቀጥሏል 09.10.2026 5分ኢትዮጵያ የኤርትራ ወታደሮች ከግዛቷ በአስቸኳይ እንዲወጡ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አመለከተች#sbsaudiopodcast -
"ኢትዮጵያ በአድዋ ጦርነት በራሷ ምድር አጥቂ እንጂ ተከላካይ አልነበረችም" ዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን 07.10.2026 26分ዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን፤ በኦስቲን ኮሙዩኒቲ ኮሌጅ ጂ አይ ኤስ ተባባሪ ፕሮፌሰር፤ ሰሞኑን "ከፑንት እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ" በሚል ርዕስ በዶ/ር ግርማ አውግቸው አርታኢነትና በሴማዊ ጥናቶች መካነ ተቋም አሳታሚነት ለሕትመት በበቃው መፅሐፍ ላይ "የአድዋ ድልና ትርክት በጂኦግራፊያዊ ዕይታ ሲፈተሽ" በሚል ርዕሰ መጠሪያ ስላቀረቡት የመጣጥፋቸው ጭብጦች ይናገራሉ።#sbsaudiopodcast -
ኢትዮጵያ በዓባይና በቀይ ባሕር ላይ ያላትን ጥቅም ዳግም አስገነዘበች፤ በትግራይ ውጊያው ቀጥሏል 06.10.2026 11分ዳግም በትረ ስልጣናቸውን የተረከቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመመስረቻ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ይፋ ንግግር፤ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት መንግሥታቸው ሁነኛ ትኩረት የሚሰጥባቸውን ዋነኛ አቅጣጫዎች አመላከቱ።#sbsaudiopodcast -
Why power is split, and how that protects you | How Australia Works - ስልጣን ስለምን ነው የተከፋፈለው፤ እንደምንስ ነው ለእርስዎ ጥበቃ የሚያደርገው | አውስትራሊያ እንደም እንደምትተገብር 06.10.2026 7分After receiving a fine for not wearing his motorbike helmet correctly, Hugo decides to have the matter heard in court. His story explains how Parliament, government and the courts have different roles, and how some official decisions can be questioned. - የሞተር ብስክሌት ሔልሜት በአግባቡ አላደረግክም በሚል አስባብ መቀጮ ሲደርሰው፤ ሁጉ ጉዳዩ ለችሎት ስሚ እንዲቀርብለት ከውሳኔ ላይ ደረሰ። የእሱ ታሪክ ፓርላማ፣ መንግሥትና ፍርድ ቤቶች ስላሏቸው የተለያዩ ሚናዎችና እንደምን የተወሰኑ ይፋ ውሳኔዎች ጥያቄ ሊቀርብባቸው እንደሚችል ግንዛቤ ያስጨብጣል።How Australia Works is an SBS podcast that uses real stories and clear explanations to help you understand how government work in Australia, how laws are made and changed, and how you can have a say. Listen to the series and find shorter versions in 60 languages on the How Australia Works main page. - አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር የ SBS ፖድካስት አውስትራሊያ ውስጥ የአውስትራሊያ መንግሥት እንደምን እንደሚንቀሳቀስ፣ ሕጎች እንደምን እንደሚቀረፁና እንደሚለወጡ፤ እርስዎም አተያይዎን እንደምን እንደሚያጋሩ እውነተኛ ታሪኮችን በመንቀስ ግንዛቤን እንዲጨብጡ የሚያግዝዎ ነው። ተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶቹን ያድምጡ፤ ቅንጭብ ዝግጅቶቹንም በ60 ቋንቋዎች አውስትራሊያ እንደምን እንደምተገብር ዋነኛ ገፅ ላይ ያግኙ። -
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና አጋሮቹ መቀሌን መቆጣጠር 05.10.2026 8分በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል እየበረታ ያለው ግጭት ያሳሰባት ዩናይትድ ስቴትስ ሁለቱ ሀገራት ከግጭት ተቆጥበው ወደ ንግግር እንዲመለሱ አሳሰበች#sbsaudiopodcast -
የአውስትራሊያ መንግሥት የከሰል ማዕድን ቁፋሮ ማስፋፋት በቅድመ COP31 ጉባኤ ተቃውሞ እየጠበቀው ነው 05.10.2026 5分አውስትራሊያ ራሷን በሰከነ የምጣኔ ሃብት ሀገርነት፣ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ መሪነትና የታዳሽ ኃይል ማዕከልነት ለማስተዋወቅ ወጥናለች#sbsaudiopodcast -
የአውስትራሊያ የቋንቋ ለውጥ የአዲሱ የSBS ክለሳ ቀራጭ ይሆናል 05.10.2026 8分በርካታ ከአንድ ቋንቋ በላይ ተናጋር የሆኑ ፍልሰተኛ ቤተሰቦች የSBS ሬዲዮ የተለያዩ ቋንቋ ፕሮግራሞችን ከማድመጥ የተያያዙ የግል ትዝታዎችና ልዩ ትስስሮሽ አሏቸው። እነዚህ ፕሮግራሞች ባለፉት ዓመታት ተለውጠዋል፤ ተስፋፍተዋል። እናም አሁን SBS በዘመናዊቷ አውስትራሊያ የሚታዩትን የማኅበረሰብ ለውጦችና ፍላጎቶችን ለማንፀባረቅ የቋንቋ አገልግሎቶቹን ክለሳ ለማካሄድ በመሰናዶ ላይ ይገኛል። ለክለሳውም የሕዝባዊ ምክክር ጊዜ ይኖራል። ይህም ከመስከረም 25 እስከ ጥቅምት 3 ድረስ ይከናወናል።#sbsaudiopodcast -
#119 Talking about hay fever (Med) - #119 Talking about hay fever (Med) 01.10.2026 10分Learn English useful for talking about hay fever. Practise everyday phrases for describing symptoms, talking about medicine, and responding kindly when someone has hay fever. - ስለ ሄይ ፊቨር (hay fever) ለመናገር እንግሊዝኛን ይማሩን ይጠቀሙ። የሕመም ምልክቶችን ገላጭ ስለሆኑ አዘቦታዊ ቃለ ሐረጎች፣ ስለ መድኃኒትና በሄይ ፊቨር የታመመን ሰው በትሁት አንደበት ማናገርን ይለማመዱ።Keep practising the phrases from this episode and test what you’ve learned with our quiz here. - ቃለ ሐረጎችን መማርን ከእዚህ ተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶች ይለማመዱና የተማሩትን እዚህይፈትኑ። -
የአውስትራሊያ መንግሥት ቬይትናም ውስጥ አንድ ለእሥር የተዳረገ ዜጋውን እንዲያስፈታ ግፊት እየተደረገበት ነው 30.09.2026 7分የአውስትራሊያ የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የብሔራዊ ባንክ የወለድ መጠን ጭማሪ ለመንግሥት የምጣኔ ሀብት አስተዳደሩ ላይ ለውጥ እንዲያካሂድ የማስጠንቀቂያ ደወል እንደሁ አመላከተ#sbsaudiopodcast -
"ኢሬቻ ለእግዚአብሔር ምስጋና የምናቀርብበት እንጂ ከሃይማኖት ጋር ግንኙነት የለውም፤ መልካም የኢሬቻ በዓል" አቶ አብደታ ሆማ 30.09.2026 13分አቶ አብደታ ሆማ፤ የቪክቶሪያ ኢሬቻ በዓል አስተባባሪ ኮሚቴ ፕሬዚደንት፤ የኢሬቻ ክብረ በዓል ሜልበርን አውስትራሊያ ውስጥ እንደምን መከበር እንደጀመረና ዘንድሮም እንደምን ተከብሮ እንደዋለ ይናገራሉ።#sbsaudiopodcast
人気の国
このポッドキャストはこれらの国のポッドキャストチャートにも登場します。