SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

SBS
Valsts Austrālija
Valoda AM
Epizodes 900
Jaunākā 17.09.2026

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Epizodes

  • "ልጆችን ቋንቋቸውንና ባሕላቸውን ማስተማር ሀብት ማውረስ ነው፤ ማንነታቸውንም ማሳወቅ ነው" ዶ/ር በላቸው ጨከነ 17.09.2026 21min
    ዶ/ር በላቸው ጨከነ የAmharicLab የጋራ መሥራች፤ በቅርቡ በይፋ የአማርኛ ቋንቋ ንባብና ፅሑፍ ስለ ጀመረው የዲጂታል መማሪያ ድረ-ገፅ አጠቃቀምና አስተምህሮት ያስረዳሉ።#sbsaudiopodcast
  • የዓለም ባንክ 'ከ90 በመቶ በላይ የኢትዮጵያ የሕክምና ተማሪዎች በሚያገኙት ስልጠና ደስተኛ አይደሉም' አለ 16.09.2026 7min
    ከ46 በመቶ በላይ የሚሆኑ የኢትዮጵያ ወጣቶች በሱስ ተጠቂዎች ናቸው ተባለ#sbsaudiopodcast
  • የንግድ ተቋማት የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት የእራሱን የኢሚግሬሽን ፖሊሲ ይፋ እንዲያደርግና የዋን ኔሽን ፖሊሲ ለምጣኔ ሃብት ድቅቀት እንደሚዳርግ አሳሰቡ 16.09.2026 5min
    የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋዛ ውስጥ ከፍርስራሾች ስር ተቀብረው የተገኙ አስከሬኖች ምናልባትም በዓለም አቀፍ ሕግ ጥሰት ሊያስፈርጁ እንደሚችል አመላከተ#sbsaudiopodcast
  • "አውስትራሊያውያን የጎዳና ተዳዳሪዎችን እየረዳን ነው፤ አግዙን፣ተባበሩን። መልካም አዲስ ዓመት!" ወ/ሮ አዳነች ገብረማሪያምና ወ/ሮ ዘነበች በፈቃዱ 16.09.2026 9min
    ወ/ሮ አዳነች ገብረማርያም የKulture Bridge መሥራችና ሊቀመንበር እና ወ/ሮ ዘነበች በቀለ የ Kulture Bridge መሥራችና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ፤ ድርጅታቸው ለአውስትራሊያውያን የጎዳና ተዳዳሪዎች እያበረከተ ስላለው የበጎ አድራጎት ሥራዎች ይናገራሉ። መስከረም 16 / ሴፕቴምበር 26 ቅዳሜ በ153 Rainbow St, Sandgate ባሰናዱት የኢትዮጵያ 2019 አዲስ ዓመት ልዩ ዝግጅት ላይም የብሪስበንና አካባቢዋ ነዋሪ ኢትዮጵያውያንና ሌሎች አፍሪካውያውያን - አውስትራሊያውያንም በሥፍራው እንዲታደሙ ይጋብዛሉ።#sbsaudiopodcast
  • "አዲሱን ዓመት በፍቅርና በአንድነት እንድናከብር እንጋብዛችኋለን" ወ/ት ገነት ማስረሻ 15.09.2026 4min
    ወ/ት ገነት ማስረሻ በቪቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ምክትል ፕሬዚደንት፤ ቅዳሜ መስከረም 9 / September 19 በ Kensington Town Hall, 30-34 Bellair St, Kensington በማኅበሩ አስተናጋጅነት ስለሚከበረው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት 2019 ልዩ የበዓል ዝግጅት ፕሮግራም ያስረዳሉ።#sbsaudiopodcast
  • የአንድ አውስትራሊያዊ አባትና ሁለት ሕፃናት ልጆች ሕይወት ባሊ - ኢንዶኔዥያ ውስጥ አለፈ 14.09.2026 6min
    የዋን ኔሽን ፓርቲ የፍልሰተኞች ቁጥር ቅነሳ ፖሊሲ ከየአቅጣጫው ብርቱ ትችት ገጠመው#sbsaudiopodcast
  • "አዲሱ ዓመት የጤና፣ የመተሰሳብና የፍቅር እንዲሆንልን፤ ሰላምንም ይዞ እንዲመጣልን ጥልቅ ምኞታችንን እንገልጣለን" በፐርዝ የኢትዮ- አውስትራሊያ መረዳጃ ዕድር 14.09.2026 3min
    አቶ ብሩክ የማ፤ በፐርዝ - ምዕራብ አውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያን የመረዳጃ ዕድር ፀሐፊ፤ ስለ ዕድሩ አመሠራረትና ተልዕኮ ያስተዋውቃሉ። የ2019 አዲስ ዓመት መልካም ምኞታቸውንም በዕድሩ ስም ያስተላልፋሉ።#sbsaudiopodcast
  • "አዲሱ አመት የታሰሩት የሚፈቱበት የተፈናቀሉት ወደቤታቸው የሚመለሱበት የወደቁት የሚነሱበት ፍቅር እና አንድነት የሚሰፍንበት የበረከት አመት ይሁንልን ።" መላክ ጸሃይ ቀሰስ መንግስቱ ሀይሌ 11.09.2026 6min
    እንኳን 2019 የኢትዮጵያውያን አዲስ አመት አደረሰን መላክ ጸሃይ መንግስቱ ሀይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ የምስራቅ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ አህጉረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ እንዲሁም የብሪዝበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ#sbsaudiopodcast
  • የዘንድሮው አዲስ አመት አይኖቻችንን ዘለአለማዊ ተስፋ ወደሚሆነው እግዚአብሄር የምናነሳበት ፤ ተስፋ የቆረጡ በአዲስ ተስፋ የሚታደሱበት ፤ እርሱን የሚፈልጉት ሁሉ የሚያሻቸውን የሚያገኙበት ይሁንልን ። ” ዶ/ር ናትናኤል ገመዳ 11.09.2026 5min
    የዘንድሮው አዲስ አመት አይኖቻችንን ዘለአለማዊ ተስፋ ወደሚሆነው እግዚአብሄር የምናነሳበት ፤ ተስፋ የቆረጡ በአዲስ ተስፋ የሚታደሱበት ፤ እርሱን የሚፈልጉት ሁሉ የሚያሻቸውን የሚያገኙበት ይሁንልን ። ” ዶ/ር ናትናኤል ገመዳ በዘጸአት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ፓስተር#sbsaudiopodcast
  • " አዲሱ አመት አዲስ ነገርን ፤ ፍቅርን ፤ መቻቻልን ፤ ጤናን እና ሰዎች የተመኙትን የሚያገኙበት ይሁንልን "- ሼክ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር 10.09.2026 2min
    አዲሱ አመት አዲስ ነገርን ፤ ፍቅርን ፤ መቻቻልን ፤ ጤናን እና ሰዎች የተመኙትን የሚያገኙበት ይሁንልን ሲሉ ሼክ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር በአውስትራሊያ የእስልምና እምነት ተከታዮች መሪ መለክታቸውን አስተላልፈዋል ::#sbsaudiopodcast
  • "መልካም የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት - ዕንቁጣጣሽ!" የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ እና የተቀዋሚ ቡድን መሪ አንገስ ቴይለር 10.09.2026 5min
    የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ እና የተቃዋሚ ቡድን መሪ አንገስ ቴይለር ለኢትዮጵያውያን አውስትራሊያውያንና ኢትዮጵያውያን የ2019 አዲስ ዓመት መልካም ምኞታቸውን ያቀርባሉ።#sbsaudiopodcast
  • አዲስ ኮከብ - ድምፃዊ ጴጥሮስ ማስረሻ 10.09.2026 27min
    በአዲስ አንፀባራቂ ኮከብነት ስሙ እየተነሳ ያለው ድምፃዊ ጴጥሮስ ማስረሻ፤ በአዲስ ዓመት ዋዜማ ከጋይንት ንፋስ መውጫ እስከ ፋና ላምሮት አይዶል አሸናፊነት እንደምን እንደበቃ ያወጋል። በ2019 አዳዲስ ዘፈኖቹን በአልበም አካትቶ ለኢትዮጵያውያን እነሆኝ ለማለት መሰናዳቱንም ያበሥራል።#sbsaudiopodcast
  • "2019 ተስፋን ይዞ፣ የደከምንበት የሚያፈራበት፣ ሐዘናችን በደስታ የሚቀየርበት፣ መከፋታችን በፈገግታ የሚተካበት ዓመት እንዲሆንልን ምኞቴ ነው" ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ 09.09.2026 4min
    ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ - የኩዊንስላንድ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፀሐፊ፤ የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት መልካም ምኞት መልዕክት።#sbsaudiopodcast
  • የሃይማኖት አባቶች የ2019 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት መልዕክት በሜልበርን - ፉትስክሬይ ፓርክ 09.09.2026 9min
    የ2019 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ቅበላ የሃይማኖት መሪዎች መልዕክትና መንፈሳዊ ዝማሬዎች ቅዳሜ ነሐሴ 30 በሜልበርን - ፉትስክሬይ ፓርክ።#sbsaudiopodcast
  • የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት የማኅበራዊ ሚዲያ ዲጂታል ደህንነት ጥበቃ ረቂቅ ሕግ በሳንሱር ተፈርጆ ትችት ተሰነዘረበት 09.09.2026 6min
    አውስትራሊያ ውስጥ የወሲባዊ ጥቃት ደረጃ መናሩ ተመለከተ#sbsaudiopodcast
  • የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) 'ሠራተኞች ማኅበራትን ማደራጀታቸውና መብታቸውን መጠየቃቸውን እንደ ተቃውሞና ችግር ፈጣሪነት መታየት የለበትም' ሲል አሳሰበ 07.09.2026 11min
    ኢትዮጵያ 100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያለው የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ተቋም ልታቋቁም ነው
  • "የመልካም አዲስ ዓመት ምኞቴን በኤምባሲው ዲፕሎማቶችና በራሴ ስም አቀርባለሁ" አቶ ያለለት ጌታቸው - በአውስትራሊያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ተወካይ ጉዳይ ፈፃሚ 07.09.2026 4min
    አቶ ያለለት ጌታቸው - በአውስትራሊያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ተወካይ ጉዳይ ፈፃሚ፤ በአውስትራሊያ ነዋሪ ለሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ አውስትራሊያውያን የ2019 አዲስ ዓመት መልካም ምኞትና የመጪ ሥራ ዘመን አገልግሎቶችን ያስመለከተ መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።
  • "የዘመን መቁጠሪያችን የሚያኮራ ልዩ ሀብታችን፤ የኢትዮጵያዊነት ልዩ ሥርዓታችንም ነው" ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ 07.09.2026 3min
    ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ የኢትዮጵያ ዘውድ ምክር ቤት ፕሬዚደንት፤ በሀገር ውስጥና በባሕር ማዶ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የ2019 አዲስ ዓመት መልካም ምኞት መልዕክት።
  • "መጪው ዓመት የሀገራችን አንድነት የሚፀናበት፤ የሰዎች ማንነት የኩራታቸው ምንጭ ብቻ የሚሆንበት ዘመን እንዲሆን እመኛለሁ።" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 07.09.2026 2min
    ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው - በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት፤ አዲሱን 2019 የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ ሕዝባዊ በዓል ምክንያት በማድረግ መልካም ምኞታቸውን ይገልጣሉ።
  • "አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያ ሀገራችን ሰላምና መረጋጋትን፤ ለወገኖቻችንም ከስጋት ነፃ የሆነ ዓመት እንዲሆን በፅኑ እመኛለሁ" ዶ/ር ለገሰ ጋረደው 07.09.2026 4min
    ዶ/ር ለገሰ ጋረደው - የደቡብ አውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ አዲሱን 2019 የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ ሕዝባዊ በዓል ምክንያት በማድረግ መልካም ምኞታቸውን ይገልጣሉ።

Populārs valstī

Šis podkasts parādās arī šo valstu podkastu topos.