SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
SBS
0
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Epizódy
-
በወሲባዊ ጥቃት ጥርጣሬ ሳቢያ በአምስት የሲድኒ ስዋንስ እግር ኳስ ተጫዋቾች ላይ ግደባ ተጣለ 19.08.2026 6minበመጪው የፀደይ ወራት በመላ አውስትራሊያ የደን ቃጠሎ ሊጨምር እንደሚችል ተመለከተ -
አዲሱ የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት በ15 ሀገሮች በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ለኢትዮጵያውያን ዜጎች መሰጠት መጀመሩን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ገለጠ 19.08.2026 9minበኢትዮጵያ 4 በመቶ የሚሆኑ ወንዶች በጡት ካንሰር ይጠቃሉ -
"ለበዓለ ደብረ ታቦር እንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰን!" መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ ጎበና 19.08.2026 10minመልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ ጎበና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሰሜን አፍሪካ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ ስለ በዓለ ደብረ ታቦር በሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አከባበር ይገልጣሉ። መንፈሳዊ ጥሪም ያቀርባሉ። -
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ኦማን ለዩናይትድ ስቴትስና ኢራን የሰላም ስምምነት ደንቃራ ከሆነች በአሜሪካ ቦምብ ልትጋይ እንደምትችል አስጠነቀቁ 18.08.2026 4minየኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ የጤና ሠራተኞች በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ያለውን የኢቦላ ወረርሽኝ ለመቋቋም ብርቱ ፈተና ገጥሟቸው እንዳለ ተመለከተ -
‘በርካታ ሠራተኞች የጡረታ አበል ተቀማጫቸውን አስቀድመው ለቤት ብድርና ኑሮ መደጎሚያ ቢያውሉት የተሻለ ሁኔታ ላይ ይሆናሉ’ የሚለው የዋን ኔሽን ዕሳቤ ተቃውሞና ድጋፍ ገጥሞታል 17.08.2026 8minሩብ ሚሊዮን ያህል አውስትራሊያውያን የምግብና ግሮሰሪ አድራሾች ለመጀመሪያ ጊዜ በሰዓት ታሳቢ ክፍያ ሊያገኙ ነው -
"ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦቻቸውን ብቻ ሳይሆን አውስትራሊያውያን ወዳጆቻቸውንም ጨምረው በአዲሱ ዓመት ዝግጅታችን ላይ እንዲገኙ እንጋብዛለን" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው 17.08.2026 22minዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው ፤ በቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ቅዳሜ ሴፕቴምበር 5 / ነሐሴ 30 በፉትስክሬይ ፓርክ ከ11: 00 am እስከ 5:00 pm ስለሚከበረው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት 2019 ቅበላ መሰናዶን አስመልክተው ይናገራሉ። -
በኢትዮጵያ የሚገነባው የቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ በቻይናና አሜሪካ ኩባንያዎች መካከል ከፍተኛ ጂኦፖለቲካዊና የንግድ ፉክክር ማዕከል ሆኗል ተባለ 17.08.2026 10minየሴት የመስተንግዶ ሠራተኞችን አለባበስና ጌጣጌጥ የሚወስነው ደንብ፤ እስከ 50 ሺህ ብር የሚደርስ መቀጮን ጨምሮ በአዲስ አበባ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ተደረገ። -
የውጭ ዜጎች በአዲስ አበባ የመኖሪያ ቤት ለመግዛት ከ150 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ያላነሰ ገንዘብ እንደሚያስፈልጋቸው አዲስ መመሪያ ወጣ 12.08.2026 9minአዲስ አበባ የድምፅ ብክለትን በሚፈጥሩ ተቋማት ላይ ከበድ ያለ ቅጣት እጥላለሁ አለች -
"ግሎባላይዜሽን አሉታዊ ጎኑ ከፍ ያለ ነው፤ ብዙ የአፍሪካ ሀገሮች የተማሩ ሰዎቻቸውን በማጣት እየተራቆቱ ነው፤ የሕዝብንም ነፃነት ነጥቋል ማለት ይቻላል" ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ 12.08.2026 27minየምጣኔ ሀብት ተመራማሪ ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ፤ የግሎባላይዜሽንን ታራካዊ ዳራ አጣቅሰው፣ በዘርፈ ብዙ ገፅታው እያሳደራቸው ስላሉት ምጣኔ ሀብታዊ፣ የቴክኖሎጂ፣ ሰብዓዊ መብቶች፣ የታዳጊ ሀገራት የአዕምሮ መራቆትና ያደጉ ሀገሮች የአዕምሮ ግኝት፣ የማንነት፣ ባሕላዊና ሃይማኖታዊ ተፅዕኖዎችን ነቅሰው ያስረዳሉ። -
የንግድ ማኅበረሰብ አባላት የፌዴራል መንግሥቱ የኢሚግሬሽን ፖሊሲን አስመልክቶ ሁነኛ ለውጦች ከማካሔዱ በፊት በጋራ እንዲመክር ጠየቁ 10.08.2026 7minፖፕ ሊዮ ሩስያና ዩክሬይን በሚያካሂዱት ጦርነት ሰላማዊ ሰዎችን ዒላማ እንዳያደርጉ አሳሰቡ -
የመሬትና ገቢዎች ተቋማትን ጨምሮ በርካታ የመንግሥት ተቋማት ውስጥ ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሆነ ማረጋገጡን የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ 10.08.2026 9minበኢትዮጵያ 79 የሚሆኑ ቋንቋዎች መኖራቸውን በጥናት ማረጋገጡን የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጠ -
2026 Census: What you need to know to ensure you’re counted - 2026 የሕዝብ ቆጠራ፤ ስለ መቆጠርዎ እርግጠኛ ለመሆን ማወቅ የሚገባዎ ምንድን ነው? 07.08.2026 10minThe 2026 Census is on Tuesday 11 August and every person in Australia on this night must be counted. Census data is used to understand where we live, the languages we use at home (including Auslan), the support we need and how Australia is changing as a nation. Being counted helps ensure your community, culture and beliefs are represented. Here’s what you need to know about completing the Census for your household. - የአውስትራሊያ 2026 ሕዝብ ቆጠራ ማክሰኞ ኦገስት 11 / ነሐሴ 5 ይከወናል። በዕለተ ምሽቱ ማንኛውም አውስትራሊያ ውስጥ ያለ ሰው በሙሉ የግድ ሊቆጠር ይገባል። የሕዝብ ቆጠራ ዳታ የት እንደምንኖር፣ ቤት ውስጥ የምንናገራቸው ቋንቋዎች ምን እንደሆኑ፣ ድጋፍ ለማድረግና አውስትራሊያ እንደ ሀገር እንደምን በመለወጥ ላይ እንዳለች ለመገንዘብ ይረዳል። መቆጠርዎ ማኅበረሰብዎ፣ ባሕልና እምነቶችዎ ውክልናን ስለማግኘታቸው ለማረጋገጥ ያግዛል። የቤትዎ ነዋሪዎች የሕዝብ ቆጠራን ሞልተው ስለማጠናቀቃቸው ማወቅ ግድ የሚልዎትን እነሆን። -
#116 Visiting a vet (Med) - #116 Visiting a vet (Med) 06.08.2026 13minLearn English useful for talking about your sick pet. Practise everyday phrases for explaining when an animal is not eating, drinking, or acting normally. - እንግሊዝኛ ይማሩ ስለ ታመመ የቤት እንሰሳዎ ለመናገር ጠቀሜታ አለው። እንሰሳት በማይመገቡበት፣ በማይጠጡበትና እንደ አዘቦታቸው በማይሆኑበት ወቅት ያንን ለመግለፅ ገላጭ ቃለ ሐረጎችን በየዕለቱ ይለማመዱ።Keep practising the phrases from this episode and test what you’ve learned with our quiz here. - ከእዚህ ክፍለ ዝግጅት የቀሰሟቸውን ቃለ ሐረጎችን ይለማመዱና እራስዎን እዚህ በዕንቆቅልሻችን ይፈትኑ። -
ጋዛ ውስጥ በእሥራኤል ጥቃት ለተገደሉ ከመቶ በላይ ፍልስጥኤማውያን የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈፀመ 05.08.2026 7minጄት ስታር ለሀገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ በረራ በእጅ ተያዥ የመንገደኞች ቀላል ሻንጣዎች ላይ የ25 ዶላር ክፍያ ሊጥል ነው -
ከኢትዮጵያ ፈጣን የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ጋር ተመጣጣኝ አዲስ የሥራ ዕድል በበቂ ሁኔታ አለመፈጠሩ ለወጣቶች ከፍተኛ የሥራ አጥነት ጫና እየፈጠረ መሆኑ ተመለከተ 05.08.2026 7minየብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም "ፋይዳ" ወደ መንግሥት ልማት ድርጅትነት መሸጋገሩን ይፋ አደረገ -
የሕዝብ ቆጠራ 2026፤ ዕለተ ቀኑ መቼ ነው? ተቆጣሪዎች እነማን ናቸው? ፋይዳውስ ምንድን ነው? 04.08.2026 3minየአውስትራሊያ ሕዝብ ቆጠራ 2026 ማክሰኞ ኦገስት 11 ምሽት ይካሔዳል። ቆጠራው አውስትራሊያውያንን ብቻ ለይቶ የሚቆጥር ሳይሆን፤ ለጉብኝት አውስትራሊያ ውስጥ የሚገኙትን፣ ዓለም አቀፍ ተማሪዎችንና በጊዜያዊ ቪዛ ያሉትን ሁሉ አካታች ነው። -
ድምፃዊና መሰንቆኛ ደርብ ዘነበ ደሳለኝ፤ ከጎንደር እስከ አውስትራሊያ 04.08.2026 12minድምፃዊና መሰንቆ ተጫዋች ደርብ ዘነበ ደሳለኝ፤ ድምፃዊት እናቱና አኮርዲዮን ተጫዋች አባቱ እንደምን የሙዚቃ ፍቅር አሳድረውበት በአምስት ዓመቱ ማንጎራጎር እንደጀመረ ያወጋል። በሀገረ አውስትራሊያ የሙዚቃ ሕይወቱ ስለ ገጠሙት ተግዳሮቶችና መልካም ዕድሎችም ይናገራል። -
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙሉ የራስ ገዝነት መብት የመዋቅር ማስተካከያ ሳቢያ ከ500 በላይ የአስተዳደር ሠራተኞችና 50 መምህራን ያለ ምደባ መቅረታቸው ተመለከተ 03.08.2026 10minለ21ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የቪዛ መዘግየት በወጣት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ላይ ከፍተኛ ስጋትን መደቀኑ ተነገረ -
How to answer the 2026 Census English proficiency question | Bonus episode - የ2026 የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ጥያቄን እንደምን መመለስ እንዳለብዎ 31.07.2026 11minHow do you choose between "not well", "well" and "very well" when the Census asks about your English? Honorary Professor Lynda Yates explains what these answers mean in everyday life, why perfect grammar isn't the goal, and how to assess your English with confidence. - በሕዝብ ቆጠራ ወቅት ስለ እንግሊዝኛ ክህሎትዎ ሲጠየቁ "አነስተኛ"፣ "ጥሩ" እና "በጣም ጥሩ" ብለው የሚመርጡት እንደምን ነው? የክብር ፕሮፌሰር ሊንዳ ዬትስ፤ እኒህ ጥያቄዎች በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ምን ማለት እንደሆኑ፣ ስሉጥ ሰዋሰው ስለምን ግብ እንዳልሆነና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታዎን እንደምን በራስው ተማምነው እንደሚመዝኑ ያስረዳሉ።Keep practising the phrases from this episode and test what you’ve learned with our quiz here. - የእዚህን ክፍለ ዝግጅት ቃለ ሐረጎች ይለማመዱና የተማሩትን በዕንቆቅልሻችን እዚህ ይሞክሩት። -
#113 Talking about winter comfort food (Med) - #113 Talking about winter comfort food (Med) 30.07.2026 8minLearn English useful for talking about cosy meals and winter comfort food. Practise everyday phrases for describing cravings, warm meals, and food that makes you feel comfortable in cold weather. - እንግሊዝኛን ይማሩ - ስለ ክረምት ሙቀት ሰጪ ምቹ ምግቦች ለመናገር ጠቀሜታ አለው። መሻትን፣ አሟቂ ምግቦችንና በብርዳማ አየር ንብረት ምቾት የሚሰጥዎትን ምግብ ለመግለጥ ፍሬ ቃሎችን በየዕለቱ ይለማመዱ።Keep practising the phrases from this episode and test what you’ve learned with our quiz here. - በእዚህ ክፍለ ዝግጅት ቃለ ፍሬዎችን መለማመዱን ይቀጥሉበት። የቀሰሙትን ዕውቅትዎንም በዕንቆቅልሻችን እዚህ ይፈትኑት።
Obľúbený v
Tento podcast sa objavuje aj v rebríčkoch podcastov týchto krajín.