ማሕደረ ዜና

ማሕደረ ዜና

DW
Land Tyskland
Genrer News, Politics, Society & Culture, Documentary
Språk AM
Avsnitt 100
Senaste 22.06.2026

ማሕደረ ዜና በየሳምንቱ ሰኞ የሚቀርብ የዜና ትንታኔ ፖድካስት ነው። በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም የተከሰቱ፣ የሚከሰቱ እና የተነገሩ ዋና ዋና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ይዳስሳል። ዝግጅቱ የሀገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማህበራትን፣ ድርጅቶችን እና ታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ የአሁን እና የወደፊት ተግባራትን በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ያቀርባል። አዘጋጁ ነጋሽ መሐመድ ነው።

Avsnitt

  • ማሕደረ ዜና፣ የ7ኛዉ አጠቃላይ ምርጫ ዉጤት፣ እድምታዉና የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ 22.06.2026 13min
    ከ5 ዓመት በፊት እንደሆነዉ ሁሉ በዘንድሮዉም ምርጫ ያሸነፈዉ ብልፅግና ፓርቲ ከትግራይ ክልል እስከ አዲስ አበባ ጠረፎች የሕዝብን ሕይወት፣ ኑሮና እንቅስቃሴ ለአደጋ ያጋለጠዉን የፀጥታ መታወክ፣ የፖለቲካ ዉዝግብ፣ ሕዝብ ያማረረዉን የኑሮ ዉድነት፣ የባለሥልጣናቱን ሙስናና የአስተዳደር እዉቀት ጉድለትን ካላሻሻለ የትናንቷ ኢትዮጵያ ዛሬ እንደሌሎች ሁሉ ዛሬ ያለችዉ ኢትዮጵያ ነገ መኖርዋ በርግጥ ያጠራጥራል።
  • ማሕደረ ዜና፣ የ7ኛዉ አጠቃላይ ምርጫ ዉጤት፣ እድምታዉና የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ 22.06.2026 13min
    ከ5 ዓመት በፊት እንደሆነዉ ሁሉ በዘንድሮዉም ምርጫ ያሸነፈዉ ብልፅግና ፓርቲ ከትግራይ ክልል እስከ አዲስ አበባ ጠረፎች የሕዝብን ሕይወት፣ ኑሮና እንቅስቃሴ ለአደጋ ያጋለጠዉን የፀጥታ መታወክ፣ የፖለቲካ ዉዝግብ፣ ሕዝብ ያማረረዉን የኑሮ ዉድነት፣ የባለሥልጣናቱን ሙስናና የአስተዳደር እዉቀት ጉድለትን ካላሻሻለ የትናንቷ ኢትዮጵያ ዛሬ እንደሌሎች ሁሉ ዛሬ ያለችዉ ኢትዮጵያ ነገ መኖርዋ በርግጥ ያጠራጥራል።
  • ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ሥምምነት-የሠላም ጭላንጭል ብርቀት 15.06.2026 12min
    ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ሆነዉ ኢራን ላይ ጦርነት የከፈቱት ጠቅላይ ሚንስትር ቢኒያሚን ኔታንኔታንያሁ በድርድሩ ሒደ,ት አልተሳተፉም ወይም ተገልለዋል።የእስራኤል የባር ኢላን ዩኒቨርስቲ የፖለካ ሳይቲስት ዮናታን ራይንሆልድ እንደሚሉት ሥምነቱ ለጠቅላይ ሚንስትር ቢኒያሚን ኔታንያሁ ፖለቲካዊ ሕይወት መጥፎ ነዉ።ኔታንያሁ አሁን የሚመኙት ተንታኙ እንዳሉት ጦርነቱ እንዲቀጥል ነዉ።
  • ማሕደረ ዜና፣ የድርድር መሐል ጦርነት፣ የጦርነት መሐል ድርድር---ዜሮ ዉጤት 08.06.2026 12min
    በአሜሪካ አማላጅነት ከሚያዚያ 16 ጀምሮ ሶስቴ ተኩስ እንዲቆም ከእስራኤል ጋር ተስማምቶ ነበር።ደቡባዊ ሊባኖስን የሚያወድመዉ የእስራኤል ጦር ድብደባ ወይም ጦርነት-ይባል ግጭት የመጫሩ ምክንያት በኢራን ላይ ጦርነት በመከፈቱ ከሆነ የኢራኑ ጦርነት ሲቆም የሊባኖሱ ያልቆመበት ምክንያት ከተጠየቀ-ትክለኛዉ መልስ «በጡንቻዉ የታበየን ማንጠይቆት» የሚል ነዉ-የሚሆነዉ።እንዲያዉ ለማለቱ ያክል ሒዝቦላሕና እስራኤል እየተዋጉ፣ የሒዝቦላሕ ጠላት እስራኤልና የሒዝቦላሕ ተቃዋሚ የቤይሩት መንግሥት፣ በሒዝቦላሕ ጠላት፣ በእስራኤል ጥብቅ ወዳጅ ዩናይትድ ስቴትስ አደራዳሪነት «ግጭትን ለማቆም» ተብዬዉን ስምምነት መዋዋላቸዉ---
  • ማሕደረ ዜና፣ ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን ይደራደራሉ፣ ይግባባሉ፣ ይዛዛታሉም 25.05.2026 13min
    ባለፈዉ ቅዳሜም የሆርሙዝ ወሽመጥ እንደሚከፈት ለዓለም ነጋዴ «እንቁልልጭ» በማለታቸዉ የነዳጅ ዘይት ዋጋ እንዲያሽቆለቁል አድርገዋል።እዉነቱ ግን «ባጭር ጊዜ» በይፋ ይደረጋል ያሉት ሥምምነት ቅዳሜም አልነበረም ዛሬም የለም።ወይም የአጭር ጊዜ ብያኔ አይታወቅም።ትራምፕ በመሐሉ ትናንት በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴያቸዉ ባሰራጩት መልዕክት ኢራን ካልተስማማች ዩናይትድ ስቴትስ ከኢራን ወደቦች በሚነሱ መርከቦች ላይ የጣለችዉን እገዳ እንደማታነሳ ዝተዋል።
  • የኢትዮጵያ እና ሱዳን ፍጥጫ ወዴት እያመራ ነው? 18.05.2026 13min
    የሱዳን ብሔራዊ ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የሚያደርጉት ውጊያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ወደሚገኝበት ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የበለጠ በመጠጋት ላይ ይገኛል። የሱዳን ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር “የሁለትዮሽ መዋቅራዊ የውይይት ማዕቀፍ” ሥምምነት የተፈራረመችው አሜሪካ በዐይነ-ቁራኛ የምትከታተለው ነው። አሜሪካ ግንቦት 24 ቀን 2018 ይካሔዳል ተብሎ ከሚጠበቀው ምርጫ በኋላ ኢትዮጵያ እና ግብጽን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ ማደራደር ትጀምራለች ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ጦርነት እንዲቀሰቀስ እንደማትሻም አስታውቃለች።
  • ማሕደረ ዜና፣ ዩናይትድ ስቴትስ-እስራኤልና ኢራን በጦርነትና ዲፕሎማሲ መሐል 11.05.2026 13min
    ለኔታንያሁ ሰበብ ሆኑ ትክክለኛ ምክንያቶች ሐመስ፣ ሒዝቦላሕ፣ሁቲ ጭፍራ፣ ኢራን ዋና የሽብር ማዕከል ናቸዉ።የዩናይትድ ስቴትስና የእስራኤል መሪዎች ዋና ጠላት የሚሏትን ኢራንን ለማንበርከክ አምና ሰኔ ሞክረዋታል።አልተሳካም።ዘንድሮ ከየካቲት ማብቂያ እስከሚያዚያ ቀጥቅጠዋታል። የትራምፕ-ኔታንያሁ ዕቅድ፣ፉከራ፣ ዛቻ ምናልባት አንዳዶች እንደሚሉት ለሽንፈት እንጂ ለድል አልበቃም።7000 ዘመናት ያስቆጠረዉን የኢራንን ሥልጣኔ ለማዉደም ትራምፕ ፎክረዉም ነበር።አልቻሉም።
  • የትግራይ ክልል አዲስ ፕሬዝደንት አዲስ ሥራ አስፈጻሚ እየጠበቀ ነው-ግጭት የማቆም ሥምምነቱስ? 04.05.2026 16min
    በህወሓት ውሳኔ መሠረት በጳጉሜ 2012 በተካሔደው እና ፌድራል መንግሥት “ሕገ-ወጥ” ባለው ምርጫ የተመሠረተው የትግራይ ክልል ምክር ቤት በመጪዎቹ ቀናት ይሰበሰባል ተብሎ ይጠበቃል። የምክር ቤቱ ወደ ሥራ መመለስም ይሁን የሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች የትግራይ ክልል እና የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ቀጣይ ግንኙነት ምን እንደሚመስል የሚበይኑ ይሆናል።
  • የሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ማኅደረ ዜና 27.04.2026 12min
  • ሱዳን “የጭካኔ ቤተ-ሙከራ” የሆነችበት ጦርነት አራተኛ ዓመቱን ጀመረ 20.04.2026 11min
    በሱዳን ጦርነት በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በድሮኖች ጥቃት ጭምር ተገድለዋል። ጦርነቱ አራተኛ ዓመቱን ሲጀምር 34 ሚሊዮን ሰዎች ሰብአዊ ርዳታ ይጠብቃሉ። ሀገሪቱን ለሁለት የከፈላትን ጦርነት ለማቆም የሚደረገው ጥረት እስካሁን አልተሳካም። ጦርነቱ ከሱዳን ድንበር በመሻገር ወደ ጎረቤት ሀገሮች ተዛምቶ “ከቁጥጥር ውጪ” ሊሆን እንደሚችል ሥጋት አለ። የሱዳን ብሔራዊ ጦር አዛዥ ሉቴናንት ጄኔራል አብዱል ፋታኅ አል-ቡርኻን እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች አዛዥ መሐመድ ሐምዳን ደጋሎ ጦርነቱን ለማቆም እስካሁን ተጨባጭ ፈቃደኝነት አላሳዩም።
  • ድርድሩ ከሽፏል ፤ ጦርነቱ ያገረሽ ይኾን ? 13.04.2026 11min
  • ማሕደረ ዜና፣ የትራምፕ ስድብና ዛቻ፣ ያበደዉ ማን ይሆን? 06.04.2026 14min
    የኢራን ትምሕርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ የመድሐኒት ፋብሪካዎች፣ ድልድዮች፣ ዩኒቨርስቲዎች ሳይቀሩ ወድመዋል።የእስራኤልና የመካከለኛዉ ምሥራቅ የአረብ ሐገራት በርካታ የኃይልና የሰላማዊ ተቋማት ተመትተዋል።ከሁሉም በላይ ምትክ የሌለዉ ከአራት ሺሕ በላይ ህይወት ጠፍቷል።በአንዳዶች ግምት በትሪሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ አንድም ጠፍቷል ሁለትም ከስሯል።ትራምፕም ግን ነገ ማክሰኞ የኢራን የመሰረተ ልማት ተቋማት የሚፈራርሱበት ቀን እንደሆነ አዉጀዋል።ባለፈዉ ሳምንት ለኢራኖች የሚገባዉ «የድጋይ ዘመን ነዉ» ያሉት ትራምፕ ትናንት ኢራኖችን «እብድ፣ ዲቃሎች» በማለትም ባደባባይ ተሳድበዋል።ያበደዉ ማን ይሆን?
  • የነዳጅ እጥረት ያስከተለው ቀውስ እና ኢትዮጵያ ልትከተለው የሚገባ ዘላቂ ስልት 30.03.2026 13min
  • እስራኤል እና አሜሪካ ከኢራን የገጠሙት ጦርነት እንዴት እና መቼ ይቆማል? 23.03.2026 12min
    ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሣምንት አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን የገጠሙት ጦርነት መቼ እንደሚቆም ሲጠየቁ “እስከ አጥንቴ ዘልቆ ሲሰማኝ” የሚል መልስ ሰጥተዋል። መልሳቸው የጦርነቱን መቋጫ ለሚናፍቁ ማስተማመኛ የሚሰጥ አይደለም። ተንታኞች 24ኛ ቀኑን ያስቆጠረው ጦርነት የሚቆምበት ጊዜ እና ሁኔታ እጅግ ውስብስብ እንደሆነ ሥጋት አላቸው።
  • ማሕደረ ዜና ፣ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን የዉጊያ ሥልትና መልስ የለሽ ጥያቄዎች 16.03.2026 14min
    የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት መንግሥት ኃይለማርያም የናደዉ ዕዝ በ1987 (እጎአ መሆኑን አይዘንጉ) ግድም አፍአበት ላይ የገጠመዉን ሽንፈት ጠላት «አካቢዉን ከበቦ ሲያበቃ የዕዙን ጭንቅላት በጠበጠዉ» ዓይነት ብለዉ ባጭሩ ገልፀዉት ነበር።የእስራኤልና የዩናይትድ ስቴትስ ጦር የካቲት 28 ጧት የኢራንን የፖለቲካ፣ የጦርና የስለላ እናትን ቆርጦ ቢጥልም ፋርሶች እንደታሰበዉ «ያልተበጠበጡበት» ሁለተኛዉ ምክንያት የጠላታቸዉን የዉጊያ ሥልት ብዙ አጥንተዉ በቅርብ አመታት ኢራቅ፣ አፍቃኒስታንና ሊቢያ ላይ ከሆነዉ ተምረዉ የነኬይን ዘመናይ ሥልት በነ አፄ ምኒልክ ጥንታዊ ሥልት ለመመከት በመዘጋጀታቸዉ ነዉ።
  • ማሕደረ ዜና፣ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ጦርነት ያስከተለዉ ምሥቅልቅል 09.03.2026 15min
    እስራኤልና ዩናይትድ ስቴትስ ኢራንን መደብደብ የጀመሩት ቴሕራን ላይ የኢራን መሪዎችን፣ ሚናብ ዉስጥ ሕፃናት ሴት ተማሪዎችን በመግደል ነዉ።መሪዎቹን ከነሚስት ልጆቻቸዉ መግደል ለቴል አቪቭ ዋሽግተን መሪዎች ራሳቸዉ ደጋግመዉ እንዳሉት ጀግንነት ነዉ።የሚናብ-ኢራን ሴት ተማሪ-አስተማሪዎችን መግደል ግን ለዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራም የቴሕራኖች ሥራ እንጂ በዓለም ተወዳዳሪ የማይገኝለት ጦራቸዉ ስሕተት ዓይደለም።
  • ማሕደረ ዜና፣ የኻምኔይ መገደል፣ የኔታናያሁ የዕድሜ ልክ ምኞትና የትራምፕ ፉከራ 02.03.2026 15min
    ሳዳም ሁሴይ፣ ኦስማ ቢን ላደን፣ ሙዓመር ቃዛፊ፣ ዑስማኢል ሐንያሕ፣ ሐሰን ነስረላሕ ሌሎችም ሲገደሉ ዓለም ከአምባገነኖች፣ከጨቋኞች እና ካሸባሪዎች መላቀቋን የቴል አቪቭ-ዋሽግተን-ለንደን-ብራስልስ መሪዎች ለዓለም አዉጀዉ ነበር።ዓለም ግን ዘንድሮም ሰላም አታዉቅም።አምና ጥር ለሁለተኛ ጊዜ የዩናይትድ ስቴትስን የፕሬዝደትነት ሥልጣን የያዙት ዶናልድ ትራምፕ የሰላም ፕሬዝደንት መሆናቸዉን ሲደሰኩሩ የልዕለ ኃያሊቱ ሐገር መሪዎች የጦርነትን አትራፊነት ብቻ ሳይሆን አስከፊነትቱን የተረዱ መስለዉ ነበር
  • ማሕደረ ዜና፣ የዩክሬን ጦርነት አራተኛ ዓመት፣ መቆሚያ አለዉ ይሆን? 23.02.2026 13min
    ዩክሬንን የሚደግፉት የምዕራባዉያን መንግሥታትና ተቋማት እንደሚሉት የሩሲያ ዕቅድ ኪቪን ባጭር ጊዜ ምናልባትም በሶስት ቀናት ዉስጥ ተቆጣጥሮ ዜለንስኪና ተባባሪዎቻቸዉን አንቆ ወደ ሞስኮ ለመዉሰድ ነበር።ፑቲን ግን ዘመቻዉ ልዩ፣ ዩክሬንን በኃይል የመግዛት ዕቅድም እንደሌላቸዉ አስታዉቀዉ ነበር።የጦርነቱ ዕቅድ ምዕራባዉያኑ እንደገመቱትም ሆነ ፑቲን እንዳሉት እስካሁን አሸናፊና ተሸናፊ አልተለየም።
  • ማሕደረ ዜና፣62ኛዉ የሙኒክ የፀጥታ ጉባኤ፣የአዉሮጳ አሜሪካኖች ልዩነት መድረክ 16.02.2026 13min
    የጀርመኑ መራሔ መንግሥት የአሜሪካ ወዳጆቻችን በቀጥታ እንዲረዱት በማለት ለጉባኤተኞች በእንግሊዘኛ ጭምር ያደረጉት ንግግር አዉሮጶች በትራምፕ አስዳደር እርምጃና መርሕ ከመስጋት አልፈዉ መናደድ፣ መቆጣታቸዉን የሚያስረዳ ነዉ።የፈረንሳይና የሌሎች የአዉሮጳ መንግሥታት መሪዎችና ተወካዮችም የፕሬዝደንት ትራምፕ አስተዳደርን በተደጋጋሚ ተችተዋል።አዉሮጳ የራስዋን የመከላከያ ኃይል ማጠናከር እንደሚገባት አሳስበዋልም።
  • ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮ-ኤርትራ ጠብ፣ የአፍሪቃ ቀንድ የሰላም ሥጋት 09.02.2026 13min
    ሮሞች፣ቱርኮች፣ፖርቱጋሎች፣ አረቦች፣ አዉሮጶች፣ሐበሾች፣ ግብፆች፣ ሶቭየት ሕብረቶች፣ ኩባዎች፣ አሜሪካኖች በየዘመናቸዉ ዘምተዉ ገድለዉ ሞተዉበታል።የዚያን ምድር ሕዝብ ደም አፋሰዉበታል።በቅርቡ ደግሞ የመካከለኛዉ ምሥራቅና የእስያ ኃያል ቱጃር መንግሥታት እየተራኮቱበት ነዉ።የአፍሪቃ ቀንድ።የጎቲንገን ዩኒቨርስቲ ባልደረባ ዶክተር ማርኩስ ፊርግል ሆነ እንደሚሉት የአፍሪቃ ቀንድ የአዲስ ቅርምትና ማዕከል ሆኗል።