ማሕደረ ዜና
DW
0
ማሕደረ ዜና በየሳምንቱ ሰኞ የሚቀርብ የዜና ትንታኔ ፖድካስት ነው። በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም የተከሰቱ፣ የሚከሰቱ እና የተነገሩ ዋና ዋና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ይዳስሳል። ዝግጅቱ የሀገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማህበራትን፣ ድርጅቶችን እና ታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ የአሁን እና የወደፊት ተግባራትን በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ያቀርባል። አዘጋጁ ነጋሽ መሐመድ ነው።
ตอน
-
ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ ጦር መቀሌን ተቆጣጠረ፣ጦርነቱ አላባራም፣አካባቢያዊዉን ማስጋቱም ቀጥሏል 05.10.2026 14นาทีከየካቲት 1981 ጀምሮ መቀሌ ከህወሓት እጅ ስትወጣ ያሁኑ ሁለተኛዋ ነዉ።የመጀመሪያዉ የፌደራሉ መንግሥት ህዳር 2013 ከተማይቱን ሲቆጣጠር ነበር።ግን ከሰባት ወር በላይ አልቆየም።ህወሓት መልሶ ተቆጣጠራት።ዘንድሮም ከመቀሌ ድል-ሽንፈት በኋላ ጦርነቱ ቦታ-ይቀይር እንጂ አላባራም -
ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያ የጦርነት ማግሥት አዲስ ጦርነት መፍለቂያ ምድር 28.09.2026 15นาทีጦርነት ሲጀመር «ተፋላሚዎች መጀመሪያ የሚገድሉት ዕዉነትን ነዉ» እንዲሉ ሆኖ የጦርነቱ ጀማሪ ማንነትን መለየት፣ እስካሁን የተገደለና የሞተዉን ሰዉ ቁጥር በዝርዝር ማወቅ አይቻልም።ተፋላሚ ኃይላት፣ ደጋፊዎቻዉ፣ መገናኛ ዘዴዎቻቸዉና በየፊናቸዉ ያደራጁት የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የፕሮፓጋንዳ ሠራዊ የሚነዙት የሐሰት መረጃ፣ስድብና ነቀፋም ቀጥሏል። -
ሑቲዎች እና ሳዑዲ አረቢያ የገጠሙት ጦርነት በደሐዋ የመን ሲቪሎችን ወደ ሰቆቃ እየገፋ ነው 21.09.2026 12นาทีየአንሳር አላሕ ንቅናቄ ከጅቡቲ 20 ኪሎ ሜትር ገደማ የምትርቀውን ማዩን ወይም ፔሪም ደሴት እና ኤርትራ ከየመን የተዋጋችባቸው የሐኒሽ ደሴቶችን ጨምሮ ከቀይ ባሕር ዳርቻ የሚገኘውን ምዕራባዊ የመን ለመቆጣጠር የፈጀበት ሣምንት ገደማ ብቻ ነው። በውጊያው ቱርክ እና ፓኪስታን ሳዑዲ አረቢያን ለመደገፍ ፈቃደኛ ቢሆኑም አሜሪካ ለጊዜው ቸልተኛ ሆናለች። -
ማሕደረ ዜና፣ የመስከረም 11፣ 2001 ጥቃት ዝክር-«ጦርነቱ ይቀጥላል» ትራምፕ 14.09.2026 14นาทีጥቃቱ ሲፈፀም ፕሬዝደንት ጆርጅ ቡሽ ሳራሶታ፣ ፍሎሪዳ የአንድ ትምሕርት ቤት ተማሪዎችን እያነጋገሩ ነበር።ፕሬዝደንቱ ከመሩት የመልዕክተኞች ጓድ ጋር አብሮ የተጓዘዉ ጋዜጠኛ ስቲቭ ሆላንድ እንደሚያስታዉሰዉ ቡሽ ከኒዮርኩ ሕንፃዎች የመጀመሪያዉ መመታቱን ሲሰሙ «የፓይለት ስሕተት ነዉ» ብለዉ ነበር።ሁለተኛዉ መደገሙ ሲነገራቸዉ ግን ፊታቸዉ ተለዋወጠ። -
የጀርመንዋ ዛክሲሶንያ ግዛት ምርጫ ዉጤት በአዉሮጳ ፖለቲካ ላይ ያለዉ አንድምታ 07.09.2026 12นาที -
ማሕደረ ዜና፣ የአሜሪካና የእስራኤል መሪዎች የጫሩት ጦርነት 6ኛ ወር 31.08.2026 14นาทีበጣም ከረዘመ በሥድት ሳምንት የቴሕራን ሥርዓትን መነቃቅሮ ለመጣል፣ የኑክሌር መርሐ-ግብሯን ለመረከብና የአሜሪካ ታማኝ ሥርዓት ቴሕራን ላይ ለመትከል የዋሽግተን-ቴል አቪቭ መሪዎች ለየሕዝባቸዉ የገቡት ቃል ግን በርግጥ በንኗል -
ማሕደረ ዜና፣ የ4 ዓመታት ዝግጅት፣የ40 ቀናት ጉባኤ-ለኢትዮጵያ ይበጅ ይሆን? 24.08.2026 21นาทีባለፈዉ ሳምንት ማብቂያ በተጠናቀቀዉ ምክክርም ህወሓትን ይዞ፣ ፋኖን፣ ኦነሠን፣ የበኒ ሻንጉል-ጉሙዝ፣ የጋምቤላ ክልሎች አማፂያንን አክሎ፣ ገሚስ-ኦብነግን፣ እንደ ኦነግ፣ ኦፌኮ የመሳሰሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን፣ ከሐገር ዉጪ የሚገኙ የፖለቲካ፣ የአካባቢ፣ የመብት ተሟጋቻች ማሕበራትን ጨምሮ አራት አመታት በፈጀዉ የምክክር ሒደት አልተካፈሉም -
ማሕደረ ዜና፣ የትራምፕ እብሪት፣ በፍርሐት የተጠፈነገዉ ዓለምና የአፍሪቃ ፈተና 17.08.2026 14นาทีየሆርሙዝ ወሽመጥ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ መዘጋቱ በተለይ አፍሪቃ በማታዉቀዉ፣በማያገባትና በማትፈልገዉ ጦርነት የርዳታ ተመፅዋች ዜጎችዋን ሕይወት እንድትከፍል አስገድዷታል።ከኢትዮጵያ እስከ ናጄሪያ፣ ከሶማሊያ እስከ ሴኔጋል የሚገኙ የአፍሪቃ ሐገራት የርዳታ እሕል፣ መድሐኒት፣ቁሳቁስ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ተቋርጦባቸዋል -
ማሕደረ ዜና፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት፣ የኃይል አሰላለፉ እንዴትነት፣ ምክንያትና መዘዙ 10.08.2026 13นาทีአፍሪቃ «የራስዋን ችግር በራስዋ መፍታት የመቻሏ» አብነት፣ ኢትዮጵያዉያን እንደሚዋጉት ሁሉ «ለሰላማዊ ዉል ለመገዛትም ፈቃደኛ የመሆናቸዉ» ምሳሌ ተደርጎ ብዙ የተነገረለት የፕሪቶሪያ ሥምምነት ተኩስ ከማስቆሙ እኩል የአዲስ የኃይል አሰላለፍ ምክንያት መሆኑ ነዉ ዚቁ።የተፋላሚ ኃይላት ዋና ተዋኞች በሥምምነቱ ይዘት፣አተረጓጎምና ገቢራዊቱ ላይ ከመነጋገር፣ ለመግባባት ከመጣር ይልቅ አጋር ፍለጋ ሲቃትቱ ከሶስት ዓመታት በላይ አስቆጥረዋል። -
ማሕደረ ዜና፣ የሸረሪና ዉጊያ፣ «የክተት» አዋጅና የፕሪቶሪያ ዉል 03.08.2026 13นาทีከሰኔ 30 በኋላ ከህወሐት ያፈነገጠዉ አንጃ አዲስ አበባ ዉስጥ የትግራይ ተወላጆችና ደጋፊዎቻቸዉን «ጦርነት አንፈልግም» በሚል በአደባባይ ሲያሰልፍ፣ መቀሌ ዉስጥ ደግሞ ህወሓት የጠራዉ ተቃራኒ ህዝባዊ ሥብሰባ ተደርጓል።ስልፍና ስብሰባዉ የቃላት ጦርነቱን ወደየደጋፊዎቻቸዉ ለማስረፅ ያለመ መሆኑ አላከራከረም። የህወሐት ዋና ፀሐፊ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር ለትግራይ ወጣቶች «አሁን ብቻችን አይደለንም» ማለታቸዉ ግን ከቃል አቀባያቸዉ አባባል ጋር የሚጣረስ በተገላቢጦሹ የጠቅላይ ሚንስትር አብይን ወቀሳ የሚያረጋግጥ ነዉ -
ማሕደረ ዜና፣ የአሜሪካና የኢራን ጦርነት-አዳዲሶቹ የጦር ግንባሮች 27.07.2026 13นาทีየዩናይትድ ስቴትስና የእስራኤል መሪዎች፣ የቴሕራኖችን ማስጠንቀቂያ ንቀዉ፣ የዲፕሎማት፣ ተንታኖችን ምክር-ማሳሰቢያ አጣጥለዉ የካቲት 28፣ 2026 ኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት በስድስተኛ ወሩ ሁለተኛ የዉጊያ ግንባር አስከፈተ። የባብ ኤል መንደብ ወሽመጥን አዘጋም።ሥልታዊዉ ወሽመጥ የአፍሪቃ፣ የእስያና የአዉሮጳ የባሕር መስመር ሕልቅት ነዉ። በባሕር ከሚተላለፉ የዓለም ሸቀጦች ከ12 ከመቶ በላይ ይመላለስበታል።ከዓለም የኢንተርኔት መስመር 17 ከመቶዉ ተዘርግቶበታል። -
ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስ ዉሳኔ፣የሶማሊያ ሠላምና የአፍሪቃ ሕብረት ተልዕኮ የመጨረሻ መጀመሪያ 20.07.2026 14นาทีየአሜሪካ ዉሳኔ ከአዉሮጳ ሕብረትና ከፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ዉሳኔዎች ጋር መቃረኑ ዋሽግተኖች ለዉሳኔዉ የሰጡትን ምክንያት አጠያያቂ አድርጎታል።አጠያየቀም-አላጠያየቀ የአሜሪካ ዉሳኔ የአፍሪቃ ዲፕሎማቶችን ጨምሮ ብዙዎች እንደሚሉት 20 ዓመት ግድም ላስቆጠረዉ ለአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊት ተልዕኮ የመጨረሻዉ መጀመሪያ ሊሆን ይችላል -
የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትና ህወሓትን ማን ወደ ድርድር ይመልሳቸዋል? 13.07.2026 11นาทีየአዲስ አበባና የመቐለ ባለሥልጣናት ለመወያየት ፍላጎት እንዳላቸው ፍንጭ ቢሰጡም በመካከላቸው ያለው እሰጥ አገባ ከፍተኛ ዕልቂትና ብርቱ ውድመት ያስከተለው ጦርነት እንዳያገረሽ የሚያሠጋ ነው። በጥቅምት 2013 ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትና ህወሓትን ወደ ድርድር ለመግፋት ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት አስፈልጓል። -
ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስ ነፃነት 250ኛ ዓመት ዝክርና ዉዝግብ 06.07.2026 15นาทีከዓለም ምጣኔ ሐብት 23 ከመቶዉን ያክል የምትቆጣጠረዉ ዩናይትድ ስቴትስ ናት።ከ31 ትሪሊዮን ዶላር በላይ።ዩናይትድ ስቴትስን በሩቅ ርቀት የምትከተለዉ ቻይና፣ ቻይናን እጅግ በጣም ርቃ የምትከተለዉ ጀርመንና ከጀርመን የምትቀጥለዉ የጃፓን ኤኮኖሚ ቢደመር የአሜሪካንን አያክልም።ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት በኋላ ሊግ ኦቭ ኔሽንስን አፍርሳ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን በሚጠቅማትና ዓላማዋን በሚያራምድ መልክ አደራጅታለች። -
ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ዉዝግብ፣ የአረቦች ሥልትና የቀይ ባሕር መዘዝ 29.06.2026 13นาทีየዋሽግተንና የቴሕራን ቁርቁስ፣ በቴል አቪቭ-ቤይሩቶች ደባ ላይ ታክሎ እንጭጩን ሥምምነት እንድም ሆርሙዝ ሰርጥ አለያም ሜድትራኒያን ባሕር ዉስጥ እንዳያሰምጠዉ ሲፈራ-ሰሞኑን፣ ቀይ ባሕር መስመር የአዲስ ሽኩቻ-ሽሚያና ግጭት መድረክ መሆኑ እየተነገረ ነዉ።አል ቁዱስ የተባለዉ የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጦር (IRGC) ክፍለ ጦር አዛዥ ብርጌድየር ጄኔራል እስማኢል ቃኒ ሐገራቸዉና ተባባሪዎችዋ አዲስ የፀጥታ መቀነት መዘርጋታቸዉን ሲናገሩ የሰማ እንጂ ያመናቸዉ ጥቂት ነበር። -
ማሕደረ ዜና፣ የ7ኛዉ አጠቃላይ ምርጫ ዉጤት፣ እድምታዉና የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ 22.06.2026 13นาทีከ5 ዓመት በፊት እንደሆነዉ ሁሉ በዘንድሮዉም ምርጫ ያሸነፈዉ ብልፅግና ፓርቲ ከትግራይ ክልል እስከ አዲስ አበባ ጠረፎች የሕዝብን ሕይወት፣ ኑሮና እንቅስቃሴ ለአደጋ ያጋለጠዉን የፀጥታ መታወክ፣ የፖለቲካ ዉዝግብ፣ ሕዝብ ያማረረዉን የኑሮ ዉድነት፣ የባለሥልጣናቱን ሙስናና የአስተዳደር እዉቀት ጉድለትን ካላሻሻለ የትናንቷ ኢትዮጵያ ዛሬ እንደሌሎች ሁሉ ዛሬ ያለችዉ ኢትዮጵያ ነገ መኖርዋ በርግጥ ያጠራጥራል። -
ማሕደረ ዜና፣ የ7ኛዉ አጠቃላይ ምርጫ ዉጤት፣ እድምታዉና የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ 22.06.2026 13นาทีከ5 ዓመት በፊት እንደሆነዉ ሁሉ በዘንድሮዉም ምርጫ ያሸነፈዉ ብልፅግና ፓርቲ ከትግራይ ክልል እስከ አዲስ አበባ ጠረፎች የሕዝብን ሕይወት፣ ኑሮና እንቅስቃሴ ለአደጋ ያጋለጠዉን የፀጥታ መታወክ፣ የፖለቲካ ዉዝግብ፣ ሕዝብ ያማረረዉን የኑሮ ዉድነት፣ የባለሥልጣናቱን ሙስናና የአስተዳደር እዉቀት ጉድለትን ካላሻሻለ የትናንቷ ኢትዮጵያ ዛሬ እንደሌሎች ሁሉ ዛሬ ያለችዉ ኢትዮጵያ ነገ መኖርዋ በርግጥ ያጠራጥራል። -
ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ሥምምነት-የሠላም ጭላንጭል ብርቀት 15.06.2026 12นาทีከዶናልድ ትራምፕ ጋር ሆነዉ ኢራን ላይ ጦርነት የከፈቱት ጠቅላይ ሚንስትር ቢኒያሚን ኔታንኔታንያሁ በድርድሩ ሒደ,ት አልተሳተፉም ወይም ተገልለዋል።የእስራኤል የባር ኢላን ዩኒቨርስቲ የፖለካ ሳይቲስት ዮናታን ራይንሆልድ እንደሚሉት ሥምነቱ ለጠቅላይ ሚንስትር ቢኒያሚን ኔታንያሁ ፖለቲካዊ ሕይወት መጥፎ ነዉ።ኔታንያሁ አሁን የሚመኙት ተንታኙ እንዳሉት ጦርነቱ እንዲቀጥል ነዉ። -
ማሕደረ ዜና፣ የድርድር መሐል ጦርነት፣ የጦርነት መሐል ድርድር---ዜሮ ዉጤት 08.06.2026 12นาทีበአሜሪካ አማላጅነት ከሚያዚያ 16 ጀምሮ ሶስቴ ተኩስ እንዲቆም ከእስራኤል ጋር ተስማምቶ ነበር።ደቡባዊ ሊባኖስን የሚያወድመዉ የእስራኤል ጦር ድብደባ ወይም ጦርነት-ይባል ግጭት የመጫሩ ምክንያት በኢራን ላይ ጦርነት በመከፈቱ ከሆነ የኢራኑ ጦርነት ሲቆም የሊባኖሱ ያልቆመበት ምክንያት ከተጠየቀ-ትክለኛዉ መልስ «በጡንቻዉ የታበየን ማንጠይቆት» የሚል ነዉ-የሚሆነዉ።እንዲያዉ ለማለቱ ያክል ሒዝቦላሕና እስራኤል እየተዋጉ፣ የሒዝቦላሕ ጠላት እስራኤልና የሒዝቦላሕ ተቃዋሚ የቤይሩት መንግሥት፣ በሒዝቦላሕ ጠላት፣ በእስራኤል ጥብቅ ወዳጅ ዩናይትድ ስቴትስ አደራዳሪነት «ግጭትን ለማቆም» ተብዬዉን ስምምነት መዋዋላቸዉ--- -
ማሕደረ ዜና፣ ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን ይደራደራሉ፣ ይግባባሉ፣ ይዛዛታሉም 25.05.2026 13นาทีባለፈዉ ቅዳሜም የሆርሙዝ ወሽመጥ እንደሚከፈት ለዓለም ነጋዴ «እንቁልልጭ» በማለታቸዉ የነዳጅ ዘይት ዋጋ እንዲያሽቆለቁል አድርገዋል።እዉነቱ ግን «ባጭር ጊዜ» በይፋ ይደረጋል ያሉት ሥምምነት ቅዳሜም አልነበረም ዛሬም የለም።ወይም የአጭር ጊዜ ብያኔ አይታወቅም።ትራምፕ በመሐሉ ትናንት በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴያቸዉ ባሰራጩት መልዕክት ኢራን ካልተስማማች ዩናይትድ ስቴትስ ከኢራን ወደቦች በሚነሱ መርከቦች ላይ የጣለችዉን እገዳ እንደማታነሳ ዝተዋል።
ยอดนิยมใน
พอดแคสต์นี้ปรากฏในชาร์ตพอดแคสต์ของประเทศเหล่านี้ด้วย