SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
SBS
0
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Bölümler
-
ሰዎች ዜጎች እንደምን ለውጥ ጠንሳሽ / ቀራጭ እንደሚሆኑና ድምፅዎ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው | አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር 20.10.2026 8dkአንድ አነስተኛ ቡድን በእርግጥ የክፍለ ከተማ ውሳኔን ማስለወጥ ይችላል? ጁሊ የማሕበረሰቧ ቤተ መጽሐፍት ሊዘጋ መሆኑን ስትሰማ፤ ከቀዬዋ ነዋሪዎች ጋር ልትታደግ ዘመቻቸውን ተቀላቀለች። ታሪኳ ፊርማዎችን በማሰባሰብ፣ የማኅበረሰብ ስብሰባዎች በመሳተፍ፣ የክፍለ ከተማ ተመራጮችን በማነጋገርና ምርጫንም በማካሔድ እንደምን በአውስትራሊያ ዲሞክራሲ ተሳታፊ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይቃኛል።አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገበር እውነተኛ ታሪኮችን ነቅሶ፤ አውስትራሊያ ውስጥ መንግሥት እንደምን እንደሚሠራ፣ ሕጎች እንደምን እንደሚቀረፁና እንደሚሻሻሉ፣ እንደምን አተያዮን ማጋራት እንደሚችሉ ግንዛቤን የሚያስጨብጥዎ የSBS ፖድካስት ነው። ተከታትይ ክፍለ ዝግጅቶችንና አጭር ክፍለ ዝግጅቶችን በ60 ቋንቋዎች አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር ዋነኛ ገፅ ላይ አግኝተው ያድምጡ። -
የፍልሰተኞች ቅነሳ ፖሊሲ አውስትራሊያን በአንድ አሠርት ዓመት ውስጥ ከአንድ ትሪሊየን ዶላር በላይ ለሆነ ጠቅላላ ብሔራዊ ዕዳ ሊዳርጋት እንደሚችል ተመለከተ 19.10.2026 7dkበሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው አዲስ ግጭት በሲቪል ዜጎች ላይ ተጨማሪ የሰብዓዊ ቀውስ ስጋት ፈጥሯል።#sbsaudiopodcast -
የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ረድኤት ማስተባበሪያ በትግራይ ክልል በርካታ ሆስፒታሎች ሥራ መጀመራቸውን አመለከተ 19.10.2026 11dkየዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያና ኤርትራ የጋራ ድንበር ላይ ጦር መከማቸት ወደ ሰፊ ቀጣናዊ ግጭት እንዳያመራ ያላቸውን ስጋት ገለጡ#sbsaudiopodcast -
"ኢትዮጵያና ኤርትራ አፋሮችን ጨምረው ለ99 ዓመት የሚዘልቅ የታላቋ አሰብ ባለስልጣን በውል ሊያቋቁሙ ይገባል" አቶ ኅሩይ ተድላ ባይሩ 17.10.2026 26dkአቶ ኅሩይ ተድላ ባይሩ፤ የቀድሞው የኤርትራ ነፃ አውጪ ግንባር (ELF) ምክትል ፕሬዚደንትና "Eritrea and Ethiopia: A front row look at issues of conflict and the potential for a peaceful resolution" መጽሐፍ ደራሲ፤ የአሰብና ሌሎችንም በኤርትራ ያሉ ሊያድጉ የሚችሉ ወደቦችንና የኢትዮጵያና ኤርትራን አሳሳቢ የጦርነት ዕሳቤ አስመልክተው ይናገራሉ። የሰላማዊ መፍትሔ ምክረ ሃሳቦቻቸውን ያጋራሉ።#sbsaudiopodcast -
የውይይት መድረክ፤ የአውስትራሊያ ሚና ለሰሜን ኢትዮጵያና ኢትዮ-ኤርትራ ግጭትና ውጥረት ቅነሳ 16.10.2026 13dkወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደስ (ኢትዮጵያዊት - አውስትራሊያዊት)፣ አቶ ልዑል ፍስሃ (ኢትዮጵያዊ - አውስትራሊያዊ)፣ እና አቶ ዮሐንስ ወንድማገኝ (ኤርትራዊ - አውስትራሊያዊ) የአውስትራሊያ መንግሥት ለኢትዮጵያና ኤርትራውያን አውስትራሊያውያን፤ ዐልፎም ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎችን በማሳደር ረገድ ለሰላም መስፈን እንደምን የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ያላቸውን ግለ አመለካከቶች ያጋራሉ።#sbsaudiopodcast -
የውይይት መድረክ፤ የኢትዮ-ኤርትራ ሉዓላዊነት፣ ብሔራዊ ጥቅምና የወደብ አጠቃቀም 16.10.2026 18dkወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደስ (ኢትዮጵያዊት - አውስትራሊያዊት)፣ አቶ ልዑል ፍስሃ (ኢትዮጵያዊ - አውስትራሊያዊ)፣ እና አቶ ዮሐንስ ወንድማገኝ (ኤርትራዊ - አውስትራሊያዊ) የኢትዮጵያና ኤርትራን ብሔራዊ ጥቅም፣ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ማስከበርን በተመለከተ አተያዮቻቸውን ያንፀባርቃሉ።#sbsaudiopodcast -
የውይይት መድረክ፤ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና የኢትዮጵያ - ኤርትራ ወታደራዊ ውጥረት ማኅበረሰባዊ የሥነ ልቦና ጫና 15.10.2026 20dkወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደስ (ኢትዮጵያዊት - አውስትራሊያዊት)፣ አቶ ልዑል ፍስሃ (ኢትዮጵያዊ - አውስትራሊያዊ)፣ እና አቶ ዮሐንስ ወንድማገኝ (ኤርትራዊ - አውስትራሊያዊ) በሰሜን ኢትዮጵያ ተከስቶ ባለው ጦርነት፤ እንዲሁም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ከርረው ያሉት ዲፕሎማሲያዊና ወታደራዊ ውጥረቶች በሀገረ አውስትራሊያ ነዋሪ በሆኑ ኢትዮጵያውንና ኤርትራውያን፤ ትውልደ - ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የማኅበረሰብ አባላት ላይ ስላሳደራቸውና ሊያሳድሯቸው ስለሚችሉት ስነ ልቦናዊ ተፅዕኖዎች ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።#sbsaudiopodcast -
በርካታ አውስትራሊያውያን መንግሥት በቤት ኪራይ ክፍያ ጭማሪ ገደብ ላይ ጣልቃ ቢገባ እንደሚሹ ገለጡ 14.10.2026 6dkበራፕ ኮከቡ ቱፓክ ሻኩር ግድያ የተከሰሰው ግለሰብ የ40 ዓመት እሥራት ተበየነበት#sbsaudiopodcast -
የተባበሩት መንግሥትታ ድርጅት የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ዓለም አቀፋዊ ይዘት እንዳይኖረው ስጋት ያደረበት መሆኑን ገለጠ 14.10.2026 11dkበኢትዮጵያ በዓመት 600 ቶን ወርቅ የማጣራት አቅም ያለው ፋብሪካ ተመረቀ#sbsaudiopodcast -
ሕጎች እንዴት ነው የሚቀረፁት፤ እርስዎ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩትስ እንደምን ነው | አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር 13.10.2026 9dkሕጎች አውስትራሊያ ውስጥ የሚቀረፁት እንደምን ነው? በዉራንጄሪው አረጋዊ አጎት ዴቭ ዋንዲን አማካይነት የቢራራንግ እንዲሁም ያራ ወንዝ በመባል የሚታወቀውን ወንዝ ታሪክ ይቅሰሙ፤ እንደምን ፅንሰ ሃሳብ ለረቂቅ ድንጋጌነት እንደበቃ፤ በቪክቶሪያ ፓርላማ ይሁንታን እንዳገኘና ንጉሣዊ ፅድቅ ተችሮት ለሕግነት እንደበቃ።አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገበር እውነተኛ ታሪኮችን ነቅሶ፤ አውስትራሊያ ውስጥ መንግሥት እንደምን እንደሚሠራ፣ ሕጎች እንደምን እንደሚቀረፁና እንደሚሻሻሉ፣ እንደምን አተያዮን ማጋራት እንደሚችሉ ግንዛቤን የሚያስጨብጥዎ የSBS ፖድካስት ነው። ተከታትይ ክፍለ ዝግጅቶችንና አጭር ክፍለ ዝግጅቶችን በ60 ቋንቋዎች አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር ዋነኛ ገፅ ላይ አግኝተው ያድምጡ። -
"የተባበሩት መንግሥታት ብዙውን ጊዜ ግጭት ማስቀረት ላይ ስኬታማ ሆኖ አላየውም፤ ግጭት ከተፈጠረ በኋላ ቶሎ ይገባል" ሌተና ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል 11.10.2026 18dkሌተና ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል፤ እ.አ.አ. ከ2012-14 በተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ባን ኪሙን ለአቢዪ እንዲሁም ከ2014-16 ለደቡብ ሱዳን የተመድ ፀጥታ ኃይል አዛዥ ሆነው ተመድበው አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ መረጃ መምሪያ ዋና ኃላፊነት ሠርተዋል፤ በቅርቡም "የግጭት አዙሪት እና የአፍሪካ ቀንድ" በሚል ርዕስ መፅሐፍ ደርሰው ለአንባቢያን አበርክተዋል። ዳግም በተቀሰቀሰው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና የኢትዮጵያና ኤርትራን ወታደራዊ የግጭት አቅጣጫ አንስተው የሙያና የተሞክሮ ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።#sbsaudiopodcast -
"በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ውጊያ መቀጠሉ የሚቀር አይመስለኝም፤ በማን የበላይነትና እንዴት ይቋጫል የሚለውን ወደፊት የምናየው ነው" ሌ/ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል 11.10.2026 17dkሌተና ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል፤ እ.አ.አ. ከ2012-14 በተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ባን ኪሙን ለአቢዪ እንዲሁም ከ2014-16 ለደቡብ ሱዳን የተመድ ፀጥታ ኃይል አዛዥ ሆነው ተመድበው አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ መረጃ መምሪያ ዋና ኃላፊነት ሠርተዋል፤ በቅርቡም "የግጭት አዙሪት እና የአፍሪካ ቀንድ" በሚል ርዕስ መፅሐፍ ደርሰው ለአንባቢያን አበርክተዋል። ዳግም በተቀሰቀሰው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና የኢትዮጵያና ኤርትራን ወታደራዊ የግጭት አቅጣጫ አንስተው የሙያና የተሞክሮ ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።#sbsaudiopodcast -
ርእሰ አድባራት ደብረሰላም መድሀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በአውስትራሊያ ያስገነባውን ሁለገብ ሕንጻ አስመረቀ 11.10.2026 15dkርእሰ አድባራት ደብረሰላም መድሀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በአውስትራሊያ ያስገነባውን ሁለገብ ሕንጻ በትናንትናው እለት አስመርቋል። የደብረሰላም ሜልበርን መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን በአውስትራሊያ የመጀመሪያ እና በአባላት መጥንም ሆነ ባገልግሎት እየሰፋ በመሄዱ ፤ የአውስትራሊያና ኒውዝላንድ ሐገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት አቡነ ሉቃስ ከሀገር አሜሪካ " ርእሰ አድባራት ደብረሰላም መድሀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በአውስትራሊያ " እንዲባል ወስነዋል። መልእክታቸውም በብጹእ አቡነ ጴጥሮስ የኒውዬርክና አካባቢው ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በኩል ተላልፏል። በምረቃው ስነ ስርአት ላይ ብጹእ አቡነ ጴጥሮስ የኒውዬርክና አካባቢው ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፤ ብፁዕ አቡነ ዬሴፍ የሲዳማ ሐገረ ስብከት ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ፤ በአውስትራሊያና ኒውዝላድ ያሉ የየደብሩ አስተዳዳሪዎችና ምእመናን ፤ የግብጽ ኮፕት ቤተክርስቲያን አባቶች፤ የፓርላማ አባላት ፤ ሚኒስትሮች ፤ የአካባቢው ከንቲባዎች እና ካውንስለሮች ተገኝተዋል።#sbsaudiopodcast -
በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የቀጥታ ጦርነት ጅማሮ ስጋት ንሯል፤ በትግራይ የጦር ኃይሎች እንቅስቃሴ ቀጥሏል 09.10.2026 5dkኢትዮጵያ የኤርትራ ወታደሮች ከግዛቷ በአስቸኳይ እንዲወጡ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አመለከተች#sbsaudiopodcast -
"ኢትዮጵያ በአድዋ ጦርነት በራሷ ምድር አጥቂ እንጂ ተከላካይ አልነበረችም" ዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን 07.10.2026 26dkዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን፤ በኦስቲን ኮሙዩኒቲ ኮሌጅ ጂ አይ ኤስ ተባባሪ ፕሮፌሰር፤ ሰሞኑን "ከፑንት እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ" በሚል ርዕስ በዶ/ር ግርማ አውግቸው አርታኢነትና በሴማዊ ጥናቶች መካነ ተቋም አሳታሚነት ለሕትመት በበቃው መፅሐፍ ላይ "የአድዋ ድልና ትርክት በጂኦግራፊያዊ ዕይታ ሲፈተሽ" በሚል ርዕሰ መጠሪያ ስላቀረቡት የመጣጥፋቸው ጭብጦች ይናገራሉ።#sbsaudiopodcast -
ኢትዮጵያ በዓባይና በቀይ ባሕር ላይ ያላትን ጥቅም ዳግም አስገነዘበች፤ በትግራይ ውጊያው ቀጥሏል 06.10.2026 11dkዳግም በትረ ስልጣናቸውን የተረከቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመመስረቻ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ይፋ ንግግር፤ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት መንግሥታቸው ሁነኛ ትኩረት የሚሰጥባቸውን ዋነኛ አቅጣጫዎች አመላከቱ።#sbsaudiopodcast -
Why power is split, and how that protects you | How Australia Works - ስልጣን ስለምን ነው የተከፋፈለው፤ እንደምንስ ነው ለእርስዎ ጥበቃ የሚያደርገው | አውስትራሊያ እንደም እንደምትተገብር 06.10.2026 7dkAfter receiving a fine for not wearing his motorbike helmet correctly, Hugo decides to have the matter heard in court. His story explains how Parliament, government and the courts have different roles, and how some official decisions can be questioned. - የሞተር ብስክሌት ሔልሜት በአግባቡ አላደረግክም በሚል አስባብ መቀጮ ሲደርሰው፤ ሁጉ ጉዳዩ ለችሎት ስሚ እንዲቀርብለት ከውሳኔ ላይ ደረሰ። የእሱ ታሪክ ፓርላማ፣ መንግሥትና ፍርድ ቤቶች ስላሏቸው የተለያዩ ሚናዎችና እንደምን የተወሰኑ ይፋ ውሳኔዎች ጥያቄ ሊቀርብባቸው እንደሚችል ግንዛቤ ያስጨብጣል።How Australia Works is an SBS podcast that uses real stories and clear explanations to help you understand how government work in Australia, how laws are made and changed, and how you can have a say. Listen to the series and find shorter versions in 60 languages on the How Australia Works main page. - አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር የ SBS ፖድካስት አውስትራሊያ ውስጥ የአውስትራሊያ መንግሥት እንደምን እንደሚንቀሳቀስ፣ ሕጎች እንደምን እንደሚቀረፁና እንደሚለወጡ፤ እርስዎም አተያይዎን እንደምን እንደሚያጋሩ እውነተኛ ታሪኮችን በመንቀስ ግንዛቤን እንዲጨብጡ የሚያግዝዎ ነው። ተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶቹን ያድምጡ፤ ቅንጭብ ዝግጅቶቹንም በ60 ቋንቋዎች አውስትራሊያ እንደምን እንደምተገብር ዋነኛ ገፅ ላይ ያግኙ። -
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና አጋሮቹ መቀሌን መቆጣጠር 05.10.2026 8dkበኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል እየበረታ ያለው ግጭት ያሳሰባት ዩናይትድ ስቴትስ ሁለቱ ሀገራት ከግጭት ተቆጥበው ወደ ንግግር እንዲመለሱ አሳሰበች#sbsaudiopodcast -
የአውስትራሊያ መንግሥት የከሰል ማዕድን ቁፋሮ ማስፋፋት በቅድመ COP31 ጉባኤ ተቃውሞ እየጠበቀው ነው 05.10.2026 5dkአውስትራሊያ ራሷን በሰከነ የምጣኔ ሃብት ሀገርነት፣ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ መሪነትና የታዳሽ ኃይል ማዕከልነት ለማስተዋወቅ ወጥናለች#sbsaudiopodcast -
የአውስትራሊያ የቋንቋ ለውጥ የአዲሱ የSBS ክለሳ ቀራጭ ይሆናል 05.10.2026 8dkበርካታ ከአንድ ቋንቋ በላይ ተናጋር የሆኑ ፍልሰተኛ ቤተሰቦች የSBS ሬዲዮ የተለያዩ ቋንቋ ፕሮግራሞችን ከማድመጥ የተያያዙ የግል ትዝታዎችና ልዩ ትስስሮሽ አሏቸው። እነዚህ ፕሮግራሞች ባለፉት ዓመታት ተለውጠዋል፤ ተስፋፍተዋል። እናም አሁን SBS በዘመናዊቷ አውስትራሊያ የሚታዩትን የማኅበረሰብ ለውጦችና ፍላጎቶችን ለማንፀባረቅ የቋንቋ አገልግሎቶቹን ክለሳ ለማካሄድ በመሰናዶ ላይ ይገኛል። ለክለሳውም የሕዝባዊ ምክክር ጊዜ ይኖራል። ይህም ከመስከረም 25 እስከ ጥቅምት 3 ድረስ ይከናወናል።#sbsaudiopodcast
Şurada popüler
Bu podcast şu ülkelerin podcast listelerinde de yer alıyor.