ሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ - Connect for Culture Africa - Ethiopia

ሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ - Connect for Culture Africa - Ethiopia

Connect for Culture Africa
Country Ethiopia
Language EN
Episodes 14
Latest 26.01.2026

የሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት በባህል እና በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ የባህላዊና የፈጠራ ኢንዱስትሪዎች ላይ ያተኮረ ነው። ከባለሙያዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት የባህልን ሚና በህብረተሰብ ውስጥ ይመረምራል። ከመንግስታዊ ድጋፍና ከስራ ፈጠራ ጀምሮ እስከ ሰላም ግንባታና ዲሞክራሲ ያሉ ጉዳዮችን ይዳስሳል። በተሾመ ወንድሙ የሚዘጋጀው ሲሆን ሁሉም ክፍሎች በአማርኛ ከእንግሊዝኛ ግርጌ ጽሑፍ ጋር ይቀርባሉ።

Episodes

  • Institutionalizing the Arts: Policy, Heritage, and Ethiopia's Creative Economy - CfCA Ethiopia - Episode 14
    Institutionalizing the Arts: Policy, Heritage, and Ethiopia's Creative Economy - CfCA Ethiopia - Episode 14 26.01.2026 1h 25m
    ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት | ክፍል 14 ሥርዓተ-ጥበብን መገንባት፦ ፖሊሲ፣ ቅርስና የኢትዮጵያ የፈጠራ ኢኮኖሚ እንግዳ፡ አቶ ሰርፀ ፍሬ ስብሐት | አዘጋጅ ተሾመ ወንድሙ በክፍል 14 ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት አዘጋጅ ተሾመ ወንድሙ የብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ከአቶ ሰርፀ ፍሬ ስብሐት ጋር ጥልቅ ውይይት ያደርጋል፡ ይህ ክፍል የኢትዮጵያን የኪነ-ጥበብ ዘርፍ ከባሕላዊና በበጎ ፈቃደኝነት ላይ ከተመሠረተ አሠራር ወጥቶ፣ ወደ ተደራጀና በፖሊሲ ወደተደገፈ ኢንዱስትሪ ለመቀየር የሚያስፈልጉ መሠረታዊ መዋቅራዊ ለውጦችን ይቃኛል፡፡ አቶ ሰርፀ የወመዘክርን ፋይዳ፣ የፖሊሲ ክፍተቶችን እና የዲጂታል ዘመኑ በፈጠራው ዘርፍ ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ በተመለከተ ተቋማዊ ራዕያቸውን ያጋራሉ፡፡ በውይይቱ ላይ የሚነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች፡ ወመዘክርን የኢኮኖሚ ሞተር ስለማድረግ፡ የታሪክና የቅርስ ማከማቻነትን ለፈጠራ ኢኮኖሚ ግብዓትነት የመጠቀም አቅም፡፡ ብሔራዊ የኪነ-...
  • Thread of Identity: Fashion as Culture and Industry | CfCA Ethiopia #13
    Thread of Identity: Fashion as Culture and Industry | CfCA Ethiopia #13 02.01.2026 57m
    ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ - ኢትዮጵያ ፖድካስት | ክፍል 13 የማንነት ክሮች - ፋሽን እንደ ባህል እና እንደ ኢንዱስትሪ እንግዳ፡ ማኅሌት ተክለ/ማርያም | አዘጋጅ ተሾመ ወንድሙ በክፍል 13 ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ - ኢትዮጵያ ፖድካስት ፤ አዝጋጅ ተሾመ ወንድሙ የሀብ ኦፍ አፍሪካ ፋሽን ዊክ መስራች እና አዘጋጅ ከሆነችው ማኅሌት ተክለ/ማርያም ጋር ውይይት ያደርጋል፡፡ ይህ ክፍል የኢትዮጵያን ፋሽን እና የፈጠራ ኢንዱስትሪ እድገት፣ተግዳሮቶችን እና መፃኢ እጣ ፈንታን ይቃኛል፡፡ ማኅሌት ከውጭ አገራት እስከ አገር ውስጥ የዘለቀ ጉዞዋን፣ በአፍሪካ ውስጥ እስከ አሁን ድረስ የዘለቀ የፋሽን መድረክን ስለመገንባቷ በተጨማሪም ስለማንነት፣ባህል እና ለፋሽን ኢንዱስትሪው ስላሉ እድሎች በውይይቱ ላይ ታጋራለች፡፡ በውይይቱ ላይ የሚነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች • ፋሽን እንደ የባህል እና የእለት ተእለት መገለጫ በኢትዮጵያ • የኢትዮጵያ እና አፍሪካ ፋሽን ኢንዱስትሪዎች እድገት • ዲዛይነሮች የሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች፡ የማምረት ሂደት፣ቁሳቁሶች፣ፖሊሲ፣ በብ...
  • The Canvas Speaks: Visual and Fine Arts in Ethiopia | CfCA Ethiopia #12
    The Canvas Speaks: Visual and Fine Arts in Ethiopia | CfCA Ethiopia #12 12.12.2025 1h 5m
    ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት፤ ክፍል 12 ''ሸራ ይናገራል፤ የእይታ ጥበባት እና ሥነ-ጥበብ በኢትዮጵያ'' እንግዳ፡ የእይታ ጥበባት አርቲስት፣ ገጣሚ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አለ የሥነ-ጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት ፕሮፌሰር፤ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን በዚህ አነቃቂና አይን ከፋች ክፍል፣ የኢትዮጵያን የእይታ ሥነ-ጥበባት እና የሥነ-ሥዕል ጥበብ ዘርፍ ጥልቀታቸውን፣ታሪካቸውን እና ተግዳሮታቸውን እንዳስሳለን፡፡ እንግዳችን ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን በሥነ-ጥበብ እና በሙዚየም ስራ ውስጥ ለበርካታ አስርት ዓመታት እንደ የፈጠራ ሰራተኛ፣መምህር እና መሪ በመሆን ያገለገሉበትን ልምድ ይዘው የቀረቡ ሲሆን በጋራ በመሆን የሚከተሉትን ጉዳዮች እንወያያለን፡፡ · በኢትዮጵያ የባህል ሥነ-ምህዳር ወስጥ የጎደለውን መሰረተ ልማት · ሙዚየሞች ለምን ከማከማቻ ስፍራነት ባለፈ ማደግ እንዳለበቸው · የመሰነድ፣የትችት እና የምርምር ጠቃሚነት · ማኅበረሰቦች ኪነ-ጥበባዊን ችሎታ እንዴት ተንከባክበው ማሳደግ እንደሚችሉ · የመንግስት ፖሊሲ፣ኢንቨስት...
  • Stages of Change: The Transformative Power of Theatre | CfCA Ethiopia #11
    Stages of Change: The Transformative Power of Theatre | CfCA Ethiopia #11 21.11.2025 56m
    ክፍል 11፡ የለውጥ መድረኮች: የትያትር ኃይል ለዘላቂ ለውጥ እንግዳ፡ መዓዛ ወርቁ፤ ጸሐፊ ተውኔት አቅራቢ፡ ተሾመ ወንድሙ በዚህ የኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት ከዝነኛዋ ጸሐፊ ተውኔት መዓዛ ወርቁ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ የባህል ተረክ ውስጥ ትያትር የተጫወተውንና እየተጫወተ ያለውን ከፍተኛ ሚና እንዳስሳለን፡፡ በትምህርት ቤቶች እና ሆቴሎች ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ፤ሀገርን ለአንድ ዓላማ እስከማስተባበር ድረስ፣መዓዛ የኢትዮጵያ ትያትር አስደማሚ ጉዞን ታስቃኘናለች፡፡ በተጨማሪም ትያትር ለፊልም፣ቴሌቪዥን፣ትምህርት፣የሀገር ግንባታ ያለውን አስተዋጽኦ እንዲሁም የጋራ ማንነትን በመቅረጽ ረገድ ያለውን አስተዋጽኦ ጸሐፊ ወደ ኋላ በመመለስ ትዳስሳለች፡፡ በዚህ ክፍል የሚከተሉትን እናነሳለን • የኢትዮጵያ ትያትር ጥልቅ ታሪክ • ትያትር በኢትዮጵያ ፊልም እና ቴሌቪዥን ላይ የሚሳተፉ ባለተሰጥኦዎችን እንዴት ኮትኩቶ እንዳሳደገ • ኪነ-ጥበብ ለህብረተሰብ እድገት እና ውይይት ለምን አስፈላጊ እንደሆነ • የፖሊሲ፣የገንዘብ ድጋፍ እና ውይይት ከ...
  • Learning the Arts: The Role of Education in Cultural Development | CfCA Ethiopia #10
    Learning the Arts: The Role of Education in Cultural Development | CfCA Ethiopia #10 31.10.2025 1h 18m
    ጥበብና ትምህርት፡ በባህል ልማት ውስጥ የትምህርት ሚና |ክፍል 10| ወደ ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት 10ኛ ክፍል እንኩዋን በደህና መጣችሁ! በዚህ ክፍል የሰላምና ሙዚቃዊ መስራች እና ዋና ዳይሬክተር ተሾመ ወንድሙ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአለ የሥነ-ጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት ምክትል ዲን/ኪዩሬተር፣ አርቲስት እንዲሁም ተመራማሪ ከሆኑት አገኘሁ አዳነ ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ህዝብ በመቅረጽ ረገድ የሥነ-ጥበብ ትምህርት ያለውን ሚና ይዳስሳሉ፡፡ የሚዳሰሱ ርዕሶች · የሥነ-ጥበብ ትምህርት ከስር መሰረት የመሰጠቱ ጥቅም · ለኢትዮጵያ ሥነ-ጥበብ የነበሩ ታሪካዊ እና ዘመናዊ አስተዋጽኦዎች · የሥነ-ጥበብ ስራዎችን ጠብቆ በማቆየት እና ሞያን በማሳደግ ረገድ ያሉ ተግዳሮቶች · ለአርቲስቶች፣ትምህርት ቤቶች እና ማኅበረሰቦች ያሉ እድሎች ይህ ክፍል ትምህርት እና ባህል በጋራ በመሆን እንዴት ብሩህ እና የሰለጠነ ህብረተሰብን እንደሚቀርጹ ለአርቲስቶች፣መምህራኖች እንዲሁም የባህል ወዳጆች እጅግ ጠቃሚ ምልከታን ይሰጣል፡፡ ይህን...
  • Owning Creativity: The State of Copyright and IPR in Ethiopia | CfCA - Ethiopia #9
    Owning Creativity: The State of Copyright and IPR in Ethiopia | CfCA - Ethiopia #9 10.10.2025 1h 3m
    ክፍል 9፡ የፈጠራ ባለቤትነት፡ የቅጂ እና የአእምሯዊ ንብረት መብት በኢትዮጵያ| ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት ይህ የኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት በኢትዮጵያ የፈጠራ ዘርፍ ውስጥ እጅግ አንገብጋቢ የሆኑትን የቅጂ መብት እና የአእምሯዊ ንብረት መብትን በጥልቀት ይዳስሳል፡፡ የሚዳሰሱ ጉዳዮች · አሁን በሚገኙ ህጎች እና ረቂቅ ፖሊሲዎች መካከል ያለው ክፍተት · የበርን ኮንቬንሽን እና ዓለም አቀፍ ፕሮቶኮሎች ጥቅም · የጋራ አስተዳደር ማኅበራት ሚና · ኢትዮጵያ ለምን አሁን ወደ ተግባር መግባት እንዳለባት · በዘርፉ የገንዘብ ድጋፍ፣ትምህርት እና ትብብር ጥቅም ይህን የባለሞያን ምልከታ የያዘውን ክፍል የፈጠራ ባለሞያዎች፣ፖሊሲ አውጪዎች፣ የባህል መሪዎች እና የአፍሪካ ባህል ተሟጋቾች ሊያዩት የሚገባ ነው፡፡ ላይክ እና ሰብስክራይብ ማድረግ አይርሱ! This episode of Connect for Culture Africa Ethiopia Podcast dives into one of the most urgent issues in E...
  • Beyond the Spotlight: Circus as a Tool for Empowerment| Teklu Ashagir | CfCA - Ethiopia #8
    Beyond the Spotlight: Circus as a Tool for Empowerment| Teklu Ashagir | CfCA - Ethiopia #8 19.09.2025 59m
    ከመድረክ ባሻገር፡ ሰርከስ እንደ አስቻይ የጥበብ ዘርፍ| ተክሉ አሻግር ከተሾመ ወንድሙ ጋር| ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት ሰላም ኢትዮጵያ ከኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ እንቅስቃሴ ጋር በጋራ ወደ ሚያቀርበው ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ኢትዮጵያ ፖድካስት እንኳን በደህና መጣችሁ፡፡ በዚህ ክፍል ተሾመ ወንድሙ ከኢትዮጵያ ሰርከስ ብሔራዊ ማኅበር ፕሬዝደንት ከተክሉ አሻግር ጋር በመሆን ሰርከስ ያለምንም ተቋማዊ ድጋፍ ወይም መሰረተ-ልማት እንዴት ህይወትን እንደለወጠ፣ወጣቶችን እንዳበቃ እንዲሁም ኢትዮጵያ በኪነ-ጥበቡ ዘርፍ ያላትን ዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ እያደረገ እንደሚገኝ አይን ገላጭ ውይይት ያካሂዳሉ፡፡ የሚዳሰሱ ርዕሶች · ኢትዮጵያ በሰርከስ ጥበብ ከዓለም አቀፍ መሪዎች መካከል የመሆኗ ሁኔታ · ከስር ጀምሮ እስከ ብቁ ባለሞያነት ድረስ ያለ ጉዞ · ሰርከስ እንደ ለውጥ እና ዲፕሎማሲ መሳሪያ · የሰርከስ ኢኮኖሚያዊ አንድምታ ይህ ውይይት ለፖሊሲ አውጪዎች፣ የፈጠራ ስራ ላይ ለተሰማሩ ሰዎች እንዲሁም ለህዝብ፤ የፈጠራ ኢንዱስትሪዎ...
  • Writing Our Truths: The State of Literature in Ethiopia - CfCA - Ethiopia #7
    Writing Our Truths: The State of Literature in Ethiopia - CfCA - Ethiopia #7 29.08.2025 1h 7m
    የሀገር ገፆች፡ የስነ-ጽሁፍ ሁኔታ በኢትዮጵያ ክፍል 7 - ሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት ደራሲ የዝና ወርቁ እና ተሾመ ወንድሙ በጋራ በመሆን በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ስነ-ጽሁፍ ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶችንና እድሎችን ይዳስሳሉ፡፡ የንባብ ልምድ ከማዳበር እስከ ፖሊሲ አስተዋጽኦ፣የህትመት ችግሮች፣ የቋንቋ ብዝኃነት እና ኢትዮጵያዊ ታሪኮችን በመግለጽ ረገድ የዘርፉ መፃኢ እጣ ፈንታ በዚህ ውይይት ይነሳሉ፡፡ የሚካተቱ ርዕሶች ዝርዝር ጸሀፊዎች በኅብረተሰብ ውስጥ ያላቸው ሚና በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ውስጥ የኢትዮጵያ የስነ-ጽሁፍ ሁኔታ ለጸሀፊዎች የመሰረተ-ልማት እና ድጋፍ ያለበት ሁኔታ ንባብን እንዲሁም መጻፍን ለማበረታታት መደረግ ስላለባቸው የማበረታቻ ስራዎች ትምህርት፣ጥልቅ ስሜት እና ተሰጥኦ ያላቸው ግንኙነት ባህልን በመጽሐፍት አማካይነት ለትውልድ ማስተላለፍ እንዲሁም ፖሊሲ እና ህትመት ያለበት ሁኔታ ይመልከቱ፣ያጋሩ እንዲሁም የውይይቱ አካል ይሁኑ! ተጨማሪ የባህል፣ፈጠራ እና ማኅበረሰብ ላይ የተዘጋጁ የፖድካስት ይዘቶች እንዲደርስዎ ላይክ፣ኮሜንት...
  • Sounds of a Nation: The Ethiopian Music Scene  - CfCA - Ethiopia #6
    Sounds of a Nation: The Ethiopian Music Scene - CfCA - Ethiopia #6 08.08.2025 1h 27m
    ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ - ኢትዮጵያ ፖድካስት | ክፍል 6 ርዕስ፡ የሀገር ድምፅ-የኢትዮጵያ ሙዚቃ ወግ እንግዳ፡ ጆርጋ መስፍን - ሳክስፎኒስት፣ሙዚቃ አቀናባሪ አዘጋጅ፡ ተሾመ ወንድሙ - የሰላም እና ሙዚቃዊ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ በዚህ የኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ - ኢትዮጵያ ፖድካስት ክፍል የኢትዮጵያን ሙዚቃ ትሩፋት፣የአሁን ተግዳሮቶቹን እንዲሁም ለወደፊት ያለውን ከፍተኛ አቅም እንዳስሳለን፡፡ እንግዳችን ጆርጋ መስፍን የኢትዮጵያ የሙዚቃ ትሩፋት ላይ በማተኮር ከቅዱስ ያሬድ እስከ ዛሬ ዘመን የሚገኘው ወጣት መር ፈጠራን ይዳስሳል፡፡ ጆርጋ መስፍንና ተሾመ ወንድሙ በጋራ በመሆን እንደ የኦሪጅናል ካሴቶች አለመኖር፣ተገቢ የክምችት ሁኔታ አለመኖር፣ጊዜ ያለፈባቸው ወይም ተደራሽ ያልሆኑ ኮንትራቶች እና ስለባህላዊ መሰረተ ልማት አስፈላጊነት ይዳስሳሉ፡፡ የሚዳሰሱ ርዕሶች ዝርዝር · ሙዚቃን ጠብቆ የማቆየት ተግዳሮቶች እና የብሔራዊ ክምትቶች መጥፋት · በሙዚቃ ኮንትራቶች እና በቅጂ መብት ጥበቃ የሚያስፈልጉ የህግ መሻሻሎች · በወጣቶች የ...
  • The Reel Story: A Conversation on Ethiopia's Film - CfCA Ethiopia #5
    The Reel Story: A Conversation on Ethiopia's Film - CfCA Ethiopia #5 18.07.2025 1h 15m
    በኢትዮጵያ ፊልም ዙሪያ ያተኮረ ውይይት| ሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት - ምእራፍ 2 ወደ ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ (ሲኤፍሲኤ) ኢትዮጵያ ፖድካስት እንኳን በደህና መጡ፤ በዚህ ክፍል በባህል እና በዘላቂ ልማት መካከል ያለውን ቁልፍ ግንኙነት እንዳስሳለን፡፡ በዚህ በኢትዮጵያ ፊልም ዙሪያ ያተኮረ ውይይት ላይ ከዝነኛው ፊልም አዘጋጅ ሄኖክ አየለ እንዲሁም ተሾመ ወንድሙ ጋር የኢትዮጵያ ፊልም ዘርፍ ላይ ወቅታዊ እና ግልጽ ውይይት እናደርጋለን፡፡ በዚህ ክፍል የሚከተሉትን ቁልፍ ጥያቄዎችን እናነሳለን፡ የኢትዮጵያ ፊልም ኢንዱስትሪ እንደ ኔትፍሊክስ ላሉ ዓለም አቀፍ መተግበሪያዎች ዝግጁ ነው? የፊልም ትምህርትን፣የገንዘብ ድጋፍን እና የፖሊሲ ትግበራን ወደ ኋላ እየጎተተው የሚገኘው ምንድነው? በፍጥነት እየተቀያየረ በሚገኝ ዲጂታል ዓለም ላይ የቅጂ መብት እንዴት ሊከበር ይችላል? በባህል ልማት ውስጥ መንግስት እና ኢንቬስተሮች ምን አይነት ሚና መጫወት አለባቸው? ከሲኒማ አዳራሾች የመጥፋት ሁኔታ አንስቶ እስከ በወጣቶች ስለሚመራ ፈጠራ እና የአገር ውስ...
  • Culture as a Catalyst for Peace, Rights, and Democracy - CfCA Ethiopia #4
    Culture as a Catalyst for Peace, Rights, and Democracy - CfCA Ethiopia #4 27.06.2025 55m
    ክፍል 3፡ የባህል ሚና ለሰላም, ሰብዓዊ መብት እና ዲሞክራሲ ግንባታ በዚህ ክፍል የባህል ተመራማሪ ከሆኑ ዶ/ር ጥላሁን በጅቷል ጋር ኪነ-ጥበብ፣ባህል እና ፈጠራ በሰላም ግንባታ፣ሕብረተሰብ ላይ ተሃድሶ በመፍጠር እንዲሁም በብሔራዊ ኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ ምን አይነት ሚና እንደሚጫወቱ እንዳስሳለን፡፡ ከባህላዊ ትሩፋቶች እስከ ዘመናዊ ኪነ-ጥበብ ድረስ ያሉትን ሁኔታዎች እንዲሁም በባህል፣በግጭት መፍታት እና በሰብዓዊ መብት መካከል ያሉትን ጥልቅ ትስስሮች ዶ/ር ጥላሁን ይተነትናሉ፡፡ በተጨማሪም የበርካታ አመታት ጥናት ላይ ተመርኩዘው ዶ/ር ጥላሁን የሚከተሉት ላይ ምልከታቸውን ያጋራሉ፡፡ · ከበፊት የተወረሱ፣ጎልተው የሚታዩ እንዲሁም ብቅ ብቅ እያሉ የሚገኙ አዳዲስ ባህሎች ሚና · ባህል በምን መልኩ የማኅበራዊ ስምምነትን ያዳብራል · የኢትዮጵያን የፈጠራ ዘርፍ ምን ተግዳሮቶች ተጋርጠውበታል · ኪነ-ጥበብ ለምን የፖሊሲ ድጋፍ እና የኢኮኖሚ ኢንቨስትመንት ያስፈልገዋል ይመልከቱ እንዲሁም አስተያየትዎን ያስፍሩ! ሰብስክራይብ ያድርጉ፤ አዳዲስ ክፍሎች ሲወ...
  • Culture as a Driver for Job Creation - CfCA Ethiopia #3
    Culture as a Driver for Job Creation - CfCA Ethiopia #3 06.06.2025 58m
    ባህል እና የባህል እና ፈጠራ ኢንዱስትሪው ላይ ለካበተ እና ጥልቅ ውይይት መድረክ በሆነው የሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት 3ኛ ክፍል ባህል ለስራ እድል ፈጠራ ያለው ሚና የሚል ውይይት ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ በተሾመ ወንድሙ ተዘጋጅቶ የሚቀርበው እና የእንግሊዝኛ የግርጌ መግለጫ ያለው ይህ ክፍል በባህል እና በስራ ቅጥር መካከል ያለውን ወሳኝ ሚና ይዳስሳል፡፡የባህል ትሩፋት የዘላቂ ስራ እና የኢኮኖሚ እድገት ምንጭ ሊሆን ይችላል? በውይይቱ የሚዳሰስ ጉዳይ ነው፡፡ ውይይቱ የኢትዮጵያን ባህል፣አፈ-ታሪክ እንዲሁም ሕብረተሰብ በማጥናት የአራት አስርት አመታት ልምድ ያላቸው ዶ/ር ባይለየኝ ጣሰው እንግዳ በመሆን የቀረቡበት ሲሆን ከተሾመ ወንድሙ ጋር በመሆን የኢትዮጵያ የባህል እሴቶች የስራ ፈጠራን፣አገር በቀል ኢኮኖሚን ለማነሳሳት እንዲሁም ማኅበረሰቦችን ለማብቃት ያላቸውን አቅም ይፈትሻሉ፡፡ ለበለጠ መረጃ ድረ-ገጻችንን https://cfcafrica.org ይጎብኙ፡፡ Culture as a Driver for Job Creation is the third episo...
  • Public Funding for the Culture and Creative Sector in Ethiopia - CfCA Ethiopia #2
    Public Funding for the Culture and Creative Sector in Ethiopia - CfCA Ethiopia #2 16.05.2025 55m
    የሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት ሁለተኛው ክፍል 'የመንግስት ድጋፍ ለባህል' የሚል ሲሆን- በባህል እና የባህል እና ፈጠራ ኢንዱስትሪ ላይ የካበቱ እና ጥልቀት ያላቸው ውይይቶች የሚካሄዱበት መድረክ ነው፡፡ በተሾመ ወንድሙ ተዘጋጅቶ ከእንግሊዝኛ የግርጌ መግለጫ ጋር የሚቀርበው ይህ ክፍል በኢትዮጵያ እንዲሁም ከዛም ባሻገር ኪነ-ጥበብን ለመደገፍ የመንግስት ድጋፍ እንዴት እንደሚመደብ ይዳስሳል፡፡በባህል ላይ የመንግስት ኢንቨስትመንት ምን ይመስላል? ተስፋ ሰጪ የሆኑ አዳዲስ ክንውንኖች ምንድን ናቸው፤ክፍተቶችስ ያሉት እምን ጋ ነው? የሚሉትን ጥያቄዎች ይመለከታል፡፡ ይህንን ውይይት የሚቀላቀሉት ዶ/ር ይስማ ጽጌ ሲሆኑ ጥናታዊ ምርምር ስራዎችን የሚሰሩት ዶ/ር ይስማ በቅርብ ጊዜ የሰሩት ጥናት በባህል ዘርፉ ላይ የመንግስት የገንዘብ ድጋፍ ምን ይመስላል የሚለው ላይ የብርሃን ጮራን የሚፈነጥቅ ነው፡፡ አቶ ተሾመ እና ዶ/ር ይስማ በጋራ የዚህን ጥናት መረጃ በጥልቀት ይመለከታሉ፣ዘላቂ የገንዘብ ድጋፍ እንዳይኖር የሚያደርጉ እንቅፋቶች እንዲሁም የለውጥ መንገዶ...
  • Defining Culture and Its Importance - Firehiwot Bayu (PhD) - CfCA Ethiopia #1
    Defining Culture and Its Importance - Firehiwot Bayu (PhD) - CfCA Ethiopia #1 25.04.2025 54m
    የባህል ምንነት እና ፋይዳው የሚለው የመጀመሪያ ክፍል የፖድካስት ዝግጅት የሲኤፍሲኤ ፖድካስት ተከታታይ ክፍሎችን መክፈቻ ዝግጅት ሲሆን ይህ ፖድካስት በባህል እና በባህላዊ እና ፈጠራ ኢንዱስትሪው ላይ ላተኮሩ የካበቱ እንዲሁም ጥልቅ ምልከታን የያዙ ውይይቶች የሚንጸባረቁበት መድረክ ነው፡፡ በዚህ በተሾመ ወንድሙ አቅራቢነት በሚቀርበው እና የእንግሊዝኛ የግርጌ መግለጫ ባለው የመክፈቻ ክፍል 'ባህል ምንድነው? ፋይዳውስ?ኅብረሰተብን በመቅረጽ ረገድ ምን ሚና ይጫወታል? እና በባህል ጥላ ስር የሚገኙት ዘርፎች ምንድናቸው?' የሚሉ መሰረታዊ ጥያቄዎችን በማንሳት መድረኩን እንከፍታለን፡፡ ዶ/ር ፍሬሕይወት ባዩ በምልከታቸው ባህል በእለት ተእለት ሕይወታችን እንዲሁም በማኅበረሰብ ላይ ያለውን ትርጉም እና አንድምታ በዝርዝር እንድመለከት በማድረግ ለውይይቱ ጥልቀት እና ትርጉም ይሰጡልናል፡፡ የበለጠ ለማወቅ የሚከተለውን ድረ-ገጽ ይጎብኙ https://cfcafrica.org Defining Culture and Its Importance launches the CfCA E...

Popular in

The podcast also appears in the podcast charts of these countries.